Wednesday, June 20, 2012

ድርሳነ ዘቅዱስ ሚካኤል



I.             ፩፦ ድርሳን ዘቅዱስ ሚካኤል

፩፦ ድርሳን ዘቅዱስ ሚካኤል
(እም ቅዱስ መጽሐፍ)

ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል

 ቅዱስ ማለት ልዩ፥ ክቡር ማለት ነው፤ ሚካኤል ማለት ደግሞ «መኑ ከመ አምላክ፥ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማነውማለት ነው። ሚካኤል የሚለው ስም ቃሉ የዕብራይስጥ ነው፤ - የሚለው «መኑ» ማለት ነው፥ - የሚለው «ከመ» ማለት ሲሆን፥ ኤል - ማለት ደግሞ «አምላክ» ማለት ነው። ይህን ማለትም የቅዱስ ሚካኤልን ስም በጠራን ቊጥር የምንመሰክረው ስለ እግዚአብሔር ነው፤ በመሆኑም እግዚአብሔርን በባሕርይ የሚመስለው፥ በሥልጣንም የሚተካከለው፥ በምድርም በሰማይም እንደሌለ የሚናገር ልዩ፥ ክቡር ስም ነው። የነቢያት አለቃ ሙሴ ባሕረ ኤርትራን ለሁለት ከፍሎ ሕዝቡን ያሻገረለትንና ፈርዖንን ከነሠራዊቱ ያሰጠመለትን አምላክ እግዚአብሔርን በመዝሙር ሲያመሰግን፥ «አቤቱ በአማልክት መካከል (በስም አማልክት ከሚባሉ፥ በስመ አማልክት ከሚጠሩ፥ አንድም አማልክት ዘበጸጋ ከተባሉ ከነቢያት ከካህናት መካከል) አንተን የሚመስል ማነው? በቅዱሳንም ዘንድ እንደ አንተ የከበረ ማነውብሏል። ዘጸ ፲፭፥፲፩። ቅዱስ ዳዊትም፦ «አቤቱ፥ ከአማልክት የሚመስልህ የለም፤» ብሏል። መዝ ፹፭፥፰።
፩፥፩፦ «ስሜ ድንቅ ነውና ለምን ትጠይቃለህመሳ ፲፫፥፲፯

Friday, June 15, 2012

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/ ማኅበረ በዓለ ወልድ ፰ኛ ዓመት ዓመታዊ ጉባኤው በአትላንታ ይከበራል

                      ". . . እስከ ሞት ድረስ የታመንክ ሁን. . ." ራዕ. ፪ ፥ ፲

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የማኅበረ በዓለ ወልድ ሰሜን አሜሪካ 
የ፳፻፬ ዓ.ም. ፰ኛ ዓመት ጉባኤውን በጆርጂያ ዋና ከተማ በሆነችው አትላንታ ላይ ሐምሌ ፳፩  እና ፳፪ (July 28 & 29, 2012) ለማክበር በዝግጅት ላይ ይገኛል። 

እርሶም ከዚህ መንፈሳዊ መዕድ ተካፋይ እንዲሆኑ በታላቅ አክብሮት ተጋብዘዋል።

የአትላንታ ማኅበረ በዓለ ወልድ ተወካዮችን ለማነጋገር
(404) 452-8550  ወይም (404) 751-8639 ደውለው ያነጋግሩ ትኬት ከቆረጡ በኃላ በሚከተለው ኢሜል አድራሻ ያሳውቁን 
atlantambw@gmail.com ወይንም eotcmbw@gmail.com ይላኩልን 

                       አምላከ ቅዱሳን አይለየን አሜን!