Wednesday, June 20, 2012

ድርሳነ ዘቅዱስ ሚካኤል



I.             ፩፦ ድርሳን ዘቅዱስ ሚካኤል

፩፦ ድርሳን ዘቅዱስ ሚካኤል
(እም ቅዱስ መጽሐፍ)

ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል

 ቅዱስ ማለት ልዩ፥ ክቡር ማለት ነው፤ ሚካኤል ማለት ደግሞ «መኑ ከመ አምላክ፥ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማነውማለት ነው። ሚካኤል የሚለው ስም ቃሉ የዕብራይስጥ ነው፤ - የሚለው «መኑ» ማለት ነው፥ - የሚለው «ከመ» ማለት ሲሆን፥ ኤል - ማለት ደግሞ «አምላክ» ማለት ነው። ይህን ማለትም የቅዱስ ሚካኤልን ስም በጠራን ቊጥር የምንመሰክረው ስለ እግዚአብሔር ነው፤ በመሆኑም እግዚአብሔርን በባሕርይ የሚመስለው፥ በሥልጣንም የሚተካከለው፥ በምድርም በሰማይም እንደሌለ የሚናገር ልዩ፥ ክቡር ስም ነው። የነቢያት አለቃ ሙሴ ባሕረ ኤርትራን ለሁለት ከፍሎ ሕዝቡን ያሻገረለትንና ፈርዖንን ከነሠራዊቱ ያሰጠመለትን አምላክ እግዚአብሔርን በመዝሙር ሲያመሰግን፥ «አቤቱ በአማልክት መካከል (በስም አማልክት ከሚባሉ፥ በስመ አማልክት ከሚጠሩ፥ አንድም አማልክት ዘበጸጋ ከተባሉ ከነቢያት ከካህናት መካከል) አንተን የሚመስል ማነው? በቅዱሳንም ዘንድ እንደ አንተ የከበረ ማነውብሏል። ዘጸ ፲፭፥፲፩። ቅዱስ ዳዊትም፦ «አቤቱ፥ ከአማልክት የሚመስልህ የለም፤» ብሏል። መዝ ፹፭፥፰።
፩፥፩፦ «ስሜ ድንቅ ነውና ለምን ትጠይቃለህመሳ ፲፫፥፲፯

Friday, June 15, 2012

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/ ማኅበረ በዓለ ወልድ ፰ኛ ዓመት ዓመታዊ ጉባኤው በአትላንታ ይከበራል

                      ". . . እስከ ሞት ድረስ የታመንክ ሁን. . ." ራዕ. ፪ ፥ ፲

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የማኅበረ በዓለ ወልድ ሰሜን አሜሪካ 
የ፳፻፬ ዓ.ም. ፰ኛ ዓመት ጉባኤውን በጆርጂያ ዋና ከተማ በሆነችው አትላንታ ላይ ሐምሌ ፳፩  እና ፳፪ (July 28 & 29, 2012) ለማክበር በዝግጅት ላይ ይገኛል። 

እርሶም ከዚህ መንፈሳዊ መዕድ ተካፋይ እንዲሆኑ በታላቅ አክብሮት ተጋብዘዋል።

የአትላንታ ማኅበረ በዓለ ወልድ ተወካዮችን ለማነጋገር
(404) 452-8550  ወይም (404) 751-8639 ደውለው ያነጋግሩ ትኬት ከቆረጡ በኃላ በሚከተለው ኢሜል አድራሻ ያሳውቁን 
atlantambw@gmail.com ወይንም eotcmbw@gmail.com ይላኩልን 

                       አምላከ ቅዱሳን አይለየን አሜን!

Wednesday, May 30, 2012

ጰራቅሊጦስ


ቤተ ክርስቲያናችን ከምታከብራቸው ዓበይት በዓላት መካከል አንዱ በዓለ ጰራቅሊጦስ ነው፡፡ ይህ በዓል ጌታችን በሚያርግበት ጊዜ ደቀመዛሙርቱን  ‹አንትሙሰ ንበሩ ሀገረ ኢየሩሳሌም እሰከ ትለብሱ ኃይለ እም አርያም ›  ሉቃ 2449 ብሏቸው አርጎ ነበር፡፡ ተናግሮ የማያስቀር ነውና ባረገ 10ኛው በተነሣ 50ኛው ቀን ጰራቅሊጦስን ሰዶላቸዋል ፡፡ 

ጰራቅሊጦስ ማለት -

1.      ናዛዚ(አጽናኝ) ማለት ነው ከመንፈስ ቅዱስ ሥራዎች አንዱ ያዘኑትን የተጨነቁትን በተለያየ ነገር ውስጥ ገብተው ግራ የተጋቡትን ሁለ ሰለሚያጽናና ናዛዚ ይባላል ፡፡
2.      ከሣቲ (ምስጢር ገላጭ) ማለት ነው የተደበቀውን የሚገልጥ የረቀቀውን የሚያገዝፍ የተሰወረውን የሚያሳይ በመሆኑ ከሣቲ ( ምስጢር ገላጭ) ይባላል ፡፡
3.      መጽንኢ (የሚያጸና) በተለያየ ሁኔታ ውስጥ ገብተው የሚባዝኑት ለመውደቅ የተፍገመገሙትን እንዳይወድቁ የሚደግፍና የሚያጸና በመሆኑ መጽንኢ (የሚያጸና) ይባላል ፡፡
4.      መንጽሂ (የሚያነጻ) ማለት ነው በኃጢአት የወደቁትን ከኃጢአታቸው የሚያነጻቸው ነውና መንጽሂ (የሚያነጻ) ይባላል ፡፡
5.      መሠተሰርየ (ይቅር ባይ )ማለት ነው በኃጢአት የወደቁትን የበደሉትን ተጸጽተው ንሰሃ ሲገቡ ይቅር የሚል በመሆኑ መሠተሰርይ ይቅር ባይ ይባላል ፡፡
6.      መስተፈሥሔ (ደስታን የሚሰጥ ) ማለት ነው የተጨነቁት፤ ያዘኑትን፤ያለቀሱትን እንባቸውን የሚያብስና ደስታን የሚሰጥ በመሆኑ መስተፈሥሔ (ደስታን የሚሰጥ) ይባላል  ፡፡

በአጠቃላይ ጰራቅሊጦስ ማለት መንፈሰ ጽድቅ ፤መንፈሰ ሕይወት ፤ባሕርያዊ እስትንፋስ አካላዊ ሕይወት ፤አካላዊ እስትንፋስ ማለት ነው፡፡

Wednesday, April 25, 2012

ትንሣኤ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አምላክ! አሜን!
“… ሕያውን ከሙታን መካከል ስለምን ትፈልጋላችሁ? ተነሥቶአል እንጂ በዚህ የለም ።ሉቃስ ፳፬ ÷
ያለውናየነበረው የሚመጣውም ከሙታንም በኵርሆኖ የተነሣው በምድርና በሰማያትያሉትን ሁሉ የሚገዛ የነፍሳችንቤዛና እረኛ በርኅራኄው ብዛትየወደደን፣ ከኃጢአታችንም በከበረ ደሙያጠበን ቅዱሱ የማርያም ልጅከባሕርይ አባቱ ከአብ፣ ከባሕርይሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋርለዘለዓለም የተመሰገነ ይሁን! አሜን!
ተሳስተንበሠራነው ኃጢአት፣ በበደላችንም ምክንያትእንደ ደረቀ ቅጠል ከመርገምናከሞት ስር ወድቀን፣ ጽድቃችንእንደመርገም ጨርቅ ሆኖ ሳለቃልኪዳኑን የማይረሳ አምላክ ከሰማያትተመለከተ። ከአቤል ጀምሮ የፈሰሰውየቅዱሳን ደም፣ ከአዳም ጀምሮየቀረበው የኃጢአት መስዋዕት የአዳምንልጅ ሊያድነው እንዳልቻለ አየ።አዳምና ልጆቹ ለብዙ ዘመናትበመንፀፈ ደይን ድቀው፤በዲያቢሎስ የባርነት ቀንበር ተይዘውበሲኦልና በግዞት መሰቃየታቸውንና ወደቀደመውርስት ለመመለስ መናፈቃቸውን አስተዋለ።ስለዚህም ከቅዱስነቱና ከክብሩ ማደሪያከጽዮን ጎበኘን።
እነሆ!የዘመኑ ፍፃሜ በደረሰ ጊዜ፣ለፍጥረቱ የሚገደው ጌታ እግዚአብሔርየመከራና የጭንቀት ቀናትን፣ የጉስቁልናናየሥቃይ፣ የጨለማና የጭጋግ ደመና ዘመናትን ያሳልፍ ዘንድ፤የተዋረደውን ሊያከብር፣ የወደቀውን ሊያነሣ፣የሞተውንም ሕይወት ይሰጥ ዘንድ፤በቸርነቱና በፍቅሩ በትህትናውም ብዛትሥጋን ለበሰ። መለኮት የሥጋንባሕርይ ገንዘብ አደረገ፣ የፈጠረውንምሥጋ ተዋሐደ። ከኃጢአትም በቀርፍፁም ሰው ሆነ። የንጋትኮከብ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስሁለተኛ ሰማይ ከሆነችው ከድንግልማርያም ተወለደ፤ የጽድቅ ፀሐይአምላክ፣ ከእውነተኛዋ ምሥራቅ ከብርሃንእናት ከድንግል ወጣ፤ በመላውዓለምም አበራ። የማይታየው ታየ፣ዘመን ዕድሜ የማይቆጠርለት ዘመንተቆጠረለት።
ዘመኑም በዕደ ዮሐንስ ተጠመቀ፤ በገዳመ ቆሮንቶስ ፵ መዓልትና ፵ ሌሊት ጾመ፤ ፈታኙንም ድል አደረገ። “ዘመኑ ተፈጸመ፤ የእግዚአብሔርም መንግሥት ቀርባለች፤ ንስሐ ግቡ፤ በወንጌልም እመኑ።” እያለ ወደገሊላ መጣ። ማርቆስ ፩÷፲፭ወንጌልን በእስራኤል አውራጃዎች ሰበከ፤በፊታቸውም ብዙ ድንቅና ተአምራትንአደረገ፤ ሕሙማንን ፈወሰ፣ ለምጻሞችንአነጻ፣ የዕውራንን ዓይን አበራ፣አንካሶች እንዲሄዱ ደንቆሮዎች እንዲሰሙ አደረገ፣ሙታንን አስነሣ። ለሰማያዊ መንግስትናለዘላለማዊ ሕይወት የሚያበቃውን የቤዛነትንቃል አስተማረ። ጥቂቶች በቃሉተመሩ፤ ብዙዎች ግን ሊያድናቸውናሊታደጋቸው ወደ አባቱም መንግሥትሊያፈልሳቸው እንደመጣ አላወቁም። ይልቁንምየአይሁድ አለቆችና ካህናት አብዝተውይቃወሙት ሊገድሉትም ያሴሩ ነበር።በምሴተ ሐሙስ እራት ከበሉበኋላ ቁጥሩና ዕድል ፈንታውከሐዋርያት ጋር የነበረው ይሁዳጌታን በመሳም ለአይሁድ አለቆችአሳልፎ ሰጠ። መስፍኑ ጲላጦስጌታ ከተከሰሰበት ጉዳይ አንዳችእውነት ባላገኘ ጊዜ ሊፈታውወደደ። የካህናት አለቆች ግንሕዝቡን አሳምፀው እንዲሰቀል ግድአሉት። ጌታም በሐሰት ፍርድለሞት ተላልፎ ተሰጠ። በመስቀልምቸነከሩት፣ እርሱ ግን የፍቅርአምላክ ነውና በመስቀል ላይሆኖም የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው በማለትቸርነቱን ገለጠላቸው። በእርሱ ቁስልእንድንፈወስ፣ በሕማሙ ድኅነት እንዲሆንልን፤ በሞቱ ሕይወትን እንድናገኝ፣በፈቃዱ ታመመ፣ መከራን ተቀበለእንጂ የሰው ልጅ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ምንም ነገርማድረግ አይቻለውም ነበር። ጌታችንናመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሙታንንያድን ዘንድ ሞተ፣ የሞትንናየዲያብሎስን ኃይል በሥልጣኑ ሽሮበሰንበት ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፤ክብርና ምሥጋና ለእርሱ ይሁን!አሜን!