በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰሜን አሜሪካ አህጉረ ስብከት ማኅበረ በዓለ ወልድ የቅዱስ ሲኖዶስ በ፲፱፺፩ ዓ.ም. ባወጣው የማኅበራት እና የሰንበት ት/ቤቶች አመሠራረት ህግ ተራ ቁጥር ፪ (ሀ) እና (መ) በመመርኮዝ የተመሠረተ መንፈሳዊ ማኅበር ነው። ማኅበሩ በተለያዩ የአሜሪካን ግዛቶች እንዲሁም በካናዳ የሚንቀሳቀስ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጥላ ስር ያለ እና የተለያዩ መንፈሳዊ ሥራዎችን ከቤተክርስቲያን ልጆች ጎን በመሆን ለመሥራት የተነሳ የክርስቲያን ወንድሞች፣ እህቶች፣ እናቶች እና አባቶች ስብስብ ነው።
Sunday, July 28, 2013
Saturday, July 27, 2013
እንኳን ለ፱ኛው ዓመታዊ ጉባኤ በሰላም አደረሰን
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ፥ አሜን።
“የአምላካችንን ቤት ከቶ አንተውም።” ነህምያ ፲፥፴፱
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርቲያን ማኅበረ በዓለ ወልድ በሰሜን አሜሪካ ፱ኛ ዓመታዊ ጉባዔ እነሆ ለመጀመሪያ ጊዜ በካናዳ ምድር ካልጋሪ ከተማ ከመላው የአሜሪካ እና የካናዳ ከተሞች በመጡ የማኅበሩ አባላት በድምቀት በመካሄድ ላይ ይገኛል።
መላው የማኅበሩ አባላትና የማኅበረ በዓለ ወልድ ወዳጆች እንኳን በሰላምና በጤና ለዚህ ቀን አደረሳችሁ። እግዚአብሔር ጉባዔውን የበረከት ያደርግልን ዘንድ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን።አሜን።
Thursday, July 18, 2013
፱ኛው ዓመታዊው የማኅበረ በዓለ ወልድ ጉባኤ ደረሰ በካልካሪ ካናዳ ዝግጅቱ ተጠናቋል
“የሚሰማም ና ይበል። የተጠማም
ይምጣ፥ የወደደም የሕይወትን ውኃ
እንዲያው ይውሰድ። “ ራዕየ ዮሐንስ ፳፪፥፲፯
ከዚህ በተጨማሪ የማኅበረ በዓለ ወልድ ካናዳ ቀጠና ላለፉት ስድስት ወራት በተከታታይ በመገናኘት ዝግጅቱን ያማረ ለማድረግ እና እግዚአብሔር የሚከብርበት ጉባኤ ለማካሄድ ደፋ ቀና ሲሉ ቆይተዋል በመሆኑም በመላው ዓለም የምንገኝ ምዕመናን በዚሁ በዓል በመገኘት የበረከቱ ተካፋይ እንድንሆን የካናዳው ማኅበረ በዓለ ወልድ በታላቅ አክብሮት ይጋብዛል።
አስታውሱ: ሐምሌ ፳፩ እና ፳፪ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. (July 27 & 28, 2013)
በሐመረ ኖሕ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን
618 – 2nd Ave NE. Calgary, Canada
ለተጨማሪ መረጃዎች በሚከተሉት ቁጥሮች ይደውሉ
403-402-7585 /
403-542-7980 / 403-975-0141
ማኅበረ በዓለ ወልድ ካናዳ
Subscribe to:
Posts (Atom)