Friday, January 13, 2012

ምሥጢረ ሥላሴ


እንኳን ለጥር ሥላሴ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

ምሥጢር
ሥሉስ ቅዱስ
አመሠጠረ ከሚለው ግስ የተገኘ ቃል ሲሆን ስውር ድብቅ ሽሽግ ማለት ሲሆን አምስቱ አዕማደ ምሥጢራትም ምሥጢር የተባሉበት ምክንያት
በሥጋዊ ጥበብ ምርምር መረዳት ስለማይቻሉ
ላመኑት እንጂ ላላመኑት ሰዎች የተሰወሩ በመሆኑ
 ምሥጢር በሁለት ይከፈላል፡፡ እነርሱም፡-
 የፈጣሪ ምሥጢር፡- ሊገለጥ የማይችል ነው፡፡ እስከ የሌለው ምሥጢርም ይባላል፡፡
 የፍጡራን ምሥጢር፡- በጊዜ የሚገለጥ /የሚታወቅ/ ነው፡፡ የሰውና የመላእክት ምሥጢር በዚህ ውስጥ የሚካተት ነው፡፡

ምሥጢረ ሥላሴ
ሥላሴ፡- የግእዝ ቃል ሲሆን ሦስትነት ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር አንድ ሲሆን ሦስት ሦስት ሲሆን አንድ ነው፡፡ ይህ የእግዚአብሔር ሦስትነት ልዩ ሦስት ነው፡፡ ሦስት ብቻ ተብሎ አይቆምምና ሦስት ሲሆን አንድም ነው፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር የአንድነት የሦስትነት ባለቤት በመሆኑ ሥላሴ ይባላል፡፡
 የእግዚአብሔር አንድነት
 እግዚአብሔር አንድ ነው ስንል በመለኮት በባሕርይ በአገዛዝ   በሥልጣን በሕላዌ /ሕልውና/ በመፍጠር በልብ በቃል በእስትንፋስ ይህን ዓለም በመፍጠር እና በማሳለፍ ይህን በመሳሰለው ነው፡፡

  በመፍጠር መዝ 10125 ዘፍ 11 ኢሳ 661-2
  በሥልጣን ዮሐ 1030

ጎንደር ደብረብርሃን ሥላሴ ቤተክርስቲያን የውስጥ ገጽታ
  በመለኮት መለኮት ማልኩት ከሚለው የዕብራይስጥ ቃል የተገኘ ሲሆን መንግስት ግዛት ማለት ነው፡፡ ይህም ለእግዚአብሔር ብቻ የተሰጠ ነው፡፡ ቆላ 29 1 ጴጥ 13
  በሕላዌ /ሕልውናአኗኗር ማለት ነው፡፡ መብለጥ መቅደም መቀዳደም የለባቸውም፡፡ ዮሐ 11-2 ዮሐ 1410

የእግዚአብሔር ልዩ ሦስትነት
 እግዚአብሔር በስም፣ በአካል፣ በግብር ሦስት ነው፡፡
 የስም ሦስትነት አብ ወልድ መንፈስቅዱስ ናቸው፡፡ ማቴ 2819፡፡
እግዚአብሔር አብ፡- ከዘለዓለም እስከዘለዓለም ከሦስቱ አካላት የአንዱ የአብ ስም ነው፡፡ 1 ጴጥ 12 ዮሐ 316
እግዚአብሔር ወልድ፡- ከዘለዓለም እስከዘለዓለም ከሦስቱ አካላት የአንዱ የወልድ ስም ነው፡፡ ወልድ ሰው በሆነ ጊዜ በተለያ ስሞች ተጠርቷል፡፡ እነዚህም፡-
        ኢየሱስ- መድኃኒት አዳኝ ማለት ነው፡፡ ማቴ 121
         ክርስቶስ- መሲሕ /ንጉሥ/ ማለት ነው፡፡ ሉቃ 211 ዮሐ 425
         አማኑኤል-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው ማለት ነው፡፡ ትን.ኢሳ 714    ማቴ 121

እግዚአብሔር ወልድ አምላክነት አስረጂ የሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ዮሐ 209 ሮሜ 1012 ዮሐ 11 ዮሐ 114 ዮሐ 2028 ዮሐ 442 የሐዋ.ሥራ 2028 ራዕይ 18 ትን.ኢሳ 96 ራዕይ 2212 ፡፡
 እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ፡- ከዘለዓም እስከ ዘለዓለም ከሦስቱ አካላት የአንዱ መንፈስ ቅዱስ ስሙ ነው፡፡
 መንፈስ ቅዱስ በተለያዩ ስሞች ይጠራል፡፡
መንፈስ- ዮሐ 35 1 ቆሮ 124 ዘፍ 12 ትን.ኢሳ 4816
የእግዚአብሔር መንፈስ - .ኢሳ 616
ጰራቅሊጦስ /አጽናኝ/ እየተባለ ይጠራል፡፡ ዮሐ 1526 ዮሐ 1416 ዮሐ 167
የእውነት መንፈስ፡፡ ዮሐ 1526

የአካል ሦስትነት
    ለአብ ፍጹም ገጽ ፍጹም መልክ ፍጹም አካል አለው፡፡
    ለወልድም ፍጹም ገጽ ፍጹም መልክ ፍጹም አካል አለው፡፡
    ለመንፈስ ቅዱስም ፍጹም ገጽ ፍጹም መልክ ፍጹም አካል አለው፡፡
የግብር ሦስትነት
የአብ ግብሩ መውለድ ማስረጽ የወልድ ግብሩ መወለድ የመንፈስ ቅዱስ ግብሩ መስረጽ ነው፡፡ አብ ወልድን ውልዷል መንፈስ ቅዱስን አስርጽዋል መንፈስ ቅዱስ ከአብ ሰርጽዋል፡፡ ወልድ ከአብ ተወልዷል ፡፡

አብ ወልድን ወለደ ማለት ከአካሉ ከባሕርይው አስገኘው ማለት ነው፡፡
ምሳሌ የሰው ነፍስ ልብነቷ /አሳቢነቷ/ ቃልነቷን እንደሚያስገኘው

ወልድ ከአብ ተወለደ ማለት አብን አክሎ አብን መስሎ ከአብ ተገኘ ማለት ነው፡፡
ምሳሌ የነፍስ ቃልነቷ ከልብ እንደተገኘ

አብ መንፈስ ቅዱስን አሰረጸው ማለት ከአካሉ ከባሕርይው አስገኘው ማለት ነው፡፡
ምሳሌ የነፍስ ልብነቷ እስትንፋስነት /ሕይወትነቷን/ እንዳስገኘ ማለት ነው

ጎንደር ደብረብርሃን ሥላሴ ቤተክርስቲያን የውጭ ገጽታ

መንፈስ ቅዱስ ከአብ ሰረጸማለት አብን አህሎ አብን መስሎ ከአብ ተገኘ ማለት ነው፡፡
ምሳሌ የነፍስ እስትንፋስነቷ ከልብ እንደተገኘ

 ይህ ማለት ግን መቀዳደም መበላለጥ አለባቸው ማለት አይደለም ፡፡

ለምሥጢረ ሥላሴ የፍጡራን ምሳሌ

የሰው ነፍስ፡- የመናገር የማሰብ ፣የመተንፈስ /የሕያውነት/ ሁኔታ አላት፡፡
ማሰብ በአብ መናገር በወልድ ሕያውነት በመንፈስ ቅዱስ ይመሰላሉ፡፡
የነፍስ ልብነቷ ቃልነቷን ሕይወትነቷን ከራሷ ታስገኛለች፡፡
ነፍስ ስትገኝ በሦስትነቷ በአንድ ጊዜ ተገኘች እንጂ ልብነቷ ቀድሞ ቃልነቷ እስትንፋስነቷ በኋላ አልተገኘም፡፡ ነፍስ በኩነታት ሦስትነት ቢኖራትም በአካል አንድ ናት፤ ሥላሴ ግን አብ አካላዊ ልብ፤ ወልድ አካላዊ ቃል መንፈስ ቅዱስ አካላዊ እስትንፋስ ነው፡፡

ፀሐይ፡- አንድ ስትሆን ሦስትነት አላት፡፡ አካሏ ብርሃኗ   ሙቀቷ ናቸው፡፡ አካሏ በአብ፣ ብርሃኗ በወልድ፣ ሙቀቷ በመንፈስ ቅዱስ ይመስላል፡፡

ባሕር፡- ስፋቱ በአብ፣ ርጥበቱ በወልድ ማዕበሉ በመንፈስ ቅዱስ ይመሰላል፡፡

ስለ ምሥጢረ ሥላሴ የማገናዘቢያ ጥቅሶች -

            በብሉይ ኪዳን    
.ኢሳ 4812 መዝ 11716 ዘኁ 624 ዘፍ 322 ፣ት.ኢሳ 63

            በሐዲስ ኪዳን
1 ቆሮ 1914 ማቴ 1715 ሉቃ322 ማቴ 2819 ማቴ 316 ዩሐ 167 የሐዋ.ሥራ 755 ዮሐ 1415 ራዕይ 141-2

በዓሉን በዓለ ሰላም በዓለ ክብር በዓለ ፍስሐ ያድርግልን - አሜን
ምንጭ: ከመልአኩ እዘዘው ብሎግ የተገኘ


No comments:

Post a Comment