Monday, October 22, 2012

ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
 ባለፈው ዝግጅታችን ስለቅዱሳን ሐዋርያት አጠቃላይ መግቢያ አቅርበን በቀጣይነትደግሞ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የእያንዳንዱን ሐዋርያ የተጋድሎ ሕይወት በዝርዝርእንደምናቀርብ ቃል ገብተን ነበር (የባለፈውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ-http://mekrez.blogspot.com/2012/09/blog-post_12.html) በመሆኑም ለዛሬየሐዋርያት አለቃ የሆነውን የሐዋርያው የቅዱስ ጴጥሮስን ሕይወትና ተጋድሎ እነሆብለናል መልካም ንባብ።

 ቅዱስ ጴጥሮስ የተወለደው በገሊላ ባሕር ዳርቻ ( የገሊላ ባሕር ስያሜዎችአሉት፡- () የገሊላ ባሕር (በገሊላ አውራጃ ስለሚገኝ) በዙሪያው ባሉ ጌንሴሬጥናጥብርያዶስ በሚባሉ ከተሞች ስም ደግሞ () ባሕረ ጌንሴሬጥ እና () ባሕረጥብርያዶስ ይባላል) ባለች ቤተሳይዳ በተባለች ከተማ ውስጥ ነው የአባቱ ስም ዮናሲሆን ትውልዱም ከነገደ ሮቤል ነው። እናቱ ደግሞ ከነገደ ስምዖን ወገን የሆነችነበረች።  በመሆኑም እንደ ኦሪት ሥርዐት ስም ሲያወጡለት በእናቱ ነገድ ስምስምዖን ብለውታል። አባቱ ዮና የያዕቆብና የዮሐንስ አባት ከሆነው ከዘብዴዎስ ጋርየሥራ ባልንጀራ ሲሆን የሁለቱም  ሥራቸው ዓሣ እያጠመዱ መሸጥ ነበር። እድሜው፭ ዓመት ሲሆን ኦሪትን እየተማረ እንዲያድግ በአቅራቢያቸው ወዳለ ወደቅፍርናሆም ምኩራብ ሰደዱት። ቅዱስ ጴጥሮስ በቅፍርናሆም እየተማረ ካደገ በኋላበዚያው ቤት ሠርቶ ኮንኮርድያ (ጴርጴቱዋየምትባል ሚስት አግብቶ እንደ አባቱዓሣ እያጠመደ በመሸጥ መኖር ጀመረ። 

 ለቅዱስ ጴጥሮስ እንድርያስ የተባለ ወንድም ነበረው። ሥራውም ልክ እንደ ወንድሙ ዓሣ ማጥመድ ነበር። ነገር ግን ይህ እንድርያስ የመጥምቀ መለኮት ቅዱስዮሐንስ ደቀ መዝሙር ነበር። መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስነዋ በግዑለእግዚአብሔር ዘየአትት ኃጢአተ ዓለም፤ እነሆ የዓለሙን ኃጢአት የሚያስወግድየእግዚአብሔር በግእያለ ስለ ክርስቶስ ሲመሰክር ሰምተው ክርስቶስን ከተከተሉትየመጀመሪያዎቹ ሁለት ሐዋርያት አንዱ ነው (፪ኛው ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ነው) /ዮሐ. : ፴፭ - / ቅዱስ ጴጥሮስ ለመጀመሪያ ጊዜ ከክርስቶስ ጋር የተዋወቀው በወንድሙ በእንድርያስግብዣ ነው። እንድርያስ ከመምህሩ ከመጥምቁ ዮሐንስ ምስክርነት ሰምቶ ክርስቶስንከተከተለ በኋላ ወዲያውኑ ለወንድሙ ለቅዱስ ጴጥሮስበትርጓሜው ክርስቶስየሚሉት መሲሕን አገኘነውበማለት ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ወስዶታል። ጌታምቅዱስ ጴጥሮስን ባየው ጊዜአንተ የዮና ልጅ ስምዖን ነህ፤ አንተ ኬፋ (ጴጥሮስ)ትባላለህአለው /ዮሐ. : ፵፪ - ፵፫/ ይህም ወደ ፊት እርሱን እንደሚከተለውናአንተ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ነህብሎ ሲመሰክር ስሙን ቀይሮአንተ ዐለት (ጴጥሮስ) ነህ …” እንሚለው ትንቢት ሲነግረው ነው /ማቴ. ፲፮ : ፲፫- /

 ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገሊላ አውራጃ እየተዘዋወረ ሲያስተምር አንድ ቀንጠዋት በጌንሴሬጥ ባሕር ወደብ ብዙ ሰዎች  ቃሉን ለመስማት ተሰበሰቡ። ጌታችንበወደቡ ሌሊቱን ሙሉ ዓሣ በማጥመድ ሥራ ሲደክሙ ያደሩ ዓሣ አጥማጆችንአገኘ። ከነዚህም መካከል ቅዱስ ጴጥሮስና ወንድሙ እንድርያስ እንዲሁም ሁለቱየዘብዴዎስ ልጆች ያዕቆብና ዮሐንስ ነበሩ። ጌታችንም ቃሉን ለመስማትየተሰበሰበውን ሕዝብ ብዛት አይቶ ከሕዝቡ ጋር ፊት ለፊት እየተያየ ለማስተማርእንዲመቸው ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ታንኳ ገብቶ በታንኳው ላይ ሆኖ ማስተማርጀመረ። ትምህርቱን ሲጨርስ ቅዱስ ጴጥሮስንመረብህን ጣልና ዓሣ ያዝአለው።ሌሊቱን ሙሉ ሲደክሙ አድረው ምንም አይነት ዓሣ አላገኙም ነበርና ቅዱስ ጴጥሮስመምህር ሆይ! ሌሊቱን ሁሉ ስንደክም አድረን ምንም አላገኘንም፤ ነገር ግንእንደቃልህ መረቡን ወደ ባሕር እንጥላለንበማለት ሳይጠራጠር መረቡን ወደ ባሕር ጣለ። በዚህ ጊዜ መጎተት እስኪያቅታቸውና እስኪደነቁ ድረስ  ጌታችን ብዙ ዓሦችወደ መረቡ እንዲገቡ አደረገ። ቅዱስ ጴጥሮስ የተደረገውን ተአምር አይቶ ከጌታችንእግር ሥር ሰገደና እንዲህ አለ፡- “እኔ ኀጢአተኛ ሰው ነኝና አቤቱ ከኔ ፈቀቅ በል” /ሉቃ. : / አባቶች ይህንን ሲተረጉሙ ቅዱስ ጴጥሮስ ይህን የተናገረውባሕርንና በውስጧ ያሉትን ፍጥረታት የሚያውቅ የእኔንማ ኀጠአት እንዴት መርምሮይፈርድብኝ ይሆን?!” ብሎ በመፍራትና ስለራሱ ኀጢአት በማሰብካንተ ጋር መኖርየማይገባኝ ኀጥእ ነኝበማለት ስለፍጹም ትሕትና ነው ይላሉ።  ጌታችን ኢየሱስክርስቶስ የቅዱስ ጴጥሮስን ፍርሃትና ድንጋጤ አይቶ፡- “ስምዖን ሆይ አትፍራ!ከእንግዲህ ወዲህ ዓሣ ሳይሆን ሰውን የምታጠምድ ትሆናለህብሎ ሁለቱንምተከተሉኝአላቸው። በዚህ ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስና ወንድሙ እንድርያስ ሁሉንትተው ተከተሉት /ሉቃ. : - ፲፩/ 

ከዚህ
ጊዜ ጀምሮ ቅዱስ ጴጥሮስ ሚስቱን፣ትዳሩን፣ ሥራውን፣ ዘመዶቹን በአጠቃላይ የዚህን ዓለም ኮተት በሙሉ እርግፍአድርጎ ትቶ ሙሉ ጊዜውን ከጌታ ጋር በማድረግ  መደበኛ ደቀ መዝሙሩ ሆነ።ለዚህም ማስረጃው በሌላ ቦታ ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታችንንሁሉን ትተን ተከተልንህ፣እንግዲህ ምን እናገኛለን?” ሲል መጠየቁና ጌታምየተከተላችሁኝ እናንተ በዳግምልደት በ፲፪ ዙፋን ትቀመጣላችሁ፤ በ፲፪ቱም ነገደ እሥራኤል ትፈርዳላችሁ።ስለስሜም ቤትን፣ ወይም ወንድሞችን፣ ወይም እኅቶችን፣ ወይም አባትን፣ ወይምእናትን፣ ወይም ሚስትን፣ ወይም ልጆችን፣ ወይም ርስትን የተወ መቶ እጥፍ ዋጋያገኛልብሎ መመለሱ ነው /ማቴ. ፲፱ : ፳፯ - ፳፱/

 ጌታችን እንደ ልማዱ በገሊላ ባሕር ዳር ባሉ መንደሮችና ከተሞች እየገባ ሲያስተምርአንድ ቀን በቤተ ሳይዳ በቅዱስ ጴጥሮስ ቤት ገብቶ አማቱን ከበሽታዋ ፈወሰለት።ይህንንም ሲያደግለት የቅዱስ ጴጥሮስ እምነት ይበልጥ ጸና፤ ልቡንም ደስ አሰኘው።
 ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታን ከተከተለ ጊዜ ጀምሮ ከዋለበት እየዋለ ካደረበት እያደረየጌታችንን ትምህርት በሚገባ ተከታትሏል። ይህ ብቻም አይደለም፤ ጌታበሚያስተምራቸው ወቅት በጥያቄና መልስ ፈጣንና ንቁ ተሳትፎም ነበረው። ጌታችንሐዋርያትን ጥያቄ ሲጠይቃቸው ብዙ ጊዜ ፈጥኖ ይመልሳል፤ እርሱም ያልገባውን ነገርለመረዳትና የሚፈልገውን ነገር ለማድረግ በተደጋጋሚ ለጌታችን ጥያቄ ያቀርብ ነበር።ጌታም በበኩሉ የተለያዩ ትዕዛዛትን ሲያዘው እንመለከታለን። ለአብነትምየተወሰኑትን ብንመለከት፡-
1. ጌታችን አምስት እንጀራና ሁለት ዓሣ አበርክቶ አምስት ሺህ ሕዝብ ሲያጠግብአይተው ሕዝቡ ይህንንስ እናንግሠው ብንራብ ያበላናል፣ ብንታመምይፈውሰናል፣ ብንሞት ያሥነሣናል በሚል ሥጋዊ አስተሳሰብ ሊያነግሡትፈለጉ። ጌታችንም ይህን ሐሳባቸውን አውቆ የመጣበት ዓላማ ይህ አይደለምናደቀ መዛሙርቱ ቀድመውት በጀልባ ተሻግረው እንዲሄዱ አድርጎ እርሱ ብቻውን ወደ ተራራ ወጥቶ መጸለይ ጀመረ። ደቀ መዛሙርቱ እንደታዘዙትበመርከብ ሲሄዱ ብርቱ ነፋስ ተነሥቶ አናወጣቸው። ባራተኛው ሰዓተሌሊት ጌታችን በባሕሩ ላይ በእግሩ ተከተላቸውና አጠገባቸው ደረሰ።በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ የማዕበሉ ብርታት ከጨለማው ጋርተዳምሮ እጅግ በተጨነቁበት ጊዜ ወደ እነርሱ የሚመጣውምትሐት ነውብለው እጅግ ተረበሹ። በዚህ ጊዜ ጌታችንአይዟችሁ አትፍሩ እኔ ነኝብሎማንነቱን ነገራቸው። ድምፁን ሰምተው ከተረጋጉ በኋላ ቅዱስ ጴጥሮስጌታሆይ አንተስ ከሆንህ በባሕሩ ላይ በእግሬ ወደ አንተ እንድመጣ እዘዘኝብሎጠየቀው። ጌታምአለው። ቅዱስ ጴጥሮስ ከመርከቡ ወረዶ መጓዝእንደጀመረ ገና በመንፈስ ቅዱስ አልታደሰም ነበርና የማዕበሉን መበርታትእይቶ ስለፈራ መስጠም ጀመረ፤ ወደ ጌታምአድነኝሲል ጮኸ። ጌታምእጁን ዘርግቶ ወደ መርከቡ ካወጣው በኋላከእኔ ጋር ሆነህ እንዴትትጠራጠራለህበሚል ገሰጸው /ማቴ. ፲፬ ፳፭ - ፴፬/

2. ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እያስተማረ ወደ ፊልጶስ ቂሣርያ ሲደርስ ሐዋርያትንበጥበብ ስለራሱ ማንነት ለማስረዳት ሲል በተዘዋዋሪ ሌሎች ሰዎች ምንእንደሚሉት ሐዋርያትን ጠየቃቸው። ሐዋርያትምአንዳንዱ መጥምቁዮሐንስ ነው፣ አንዳንዱ ኤልያስ ነው፥ ሌሎች ደግሞ ከነቢያት አንዱ ነውይሉሃልሲሉ መለሱለት። ጌታችንምለመሆኑ እናንተስ ምን ትሉኛላችሁብሎ ስለ እርሱ ያላቸውን ግንዛቤ ጠየቃቸው። በዚህ ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስአንተ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ነህሲል መሰከረ። ጌታችንኢየሱስ ክርስቶስየእኔ ትክክለኛ ማንነት ሌሎች(አይሁድ) እንዳሉት ሳይሆንቅዱስ ጴጥሮስ እንዳለው (እንደተናገረው) ነውበማለት ቅዱስ ጴጥሮስንእጅግ አድርጎ አመስግኖታል:- “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ አንተ ብፁዕ ነህ፤በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና። እኔምእልሃለሁ፥ አንተ ዐለት ነህ፥ በዚያች ዐለት ላይም ቤተ ክርስቲያኔንእሠራታለሁ፥ የሲኦል በሮችም አይበረታቱባትም” /ማቴ. ፲፮   ፲፫ - ፲፱/።ቅዱስ ጴጥሮስ የክርስቶስን የባሕርይ አምላክነት ከመሰከረ በኋላ ጌታችንስሙን ቀይሮለታል። ስምዖን ይባል የነበረውዐለትተባለ (በዕብራይጥኬፋ፣ በጽርዕ(ግሪክ) ጴጥሮስ፣ በግዕዝ ኰኵሕ በአማርኛ ዐለት ማለትነው)  ጌታ በዚህች ዐለት ላይ ቤተክርስቲያኑን እንደሚሠራትም ተናግሯል።ይህም ማለት ቤተክርስቲያን የምትመሠረተው በቅዱስ ጴጥሮስ ሃይማኖት ማለትም በክርስቶስ ማንነት ላይ ባለ ትክክለኛ እምነት ነው ማለት ነው።እርሱምጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስመሆኑን ጠንቅቆ ማመን ነው። ሁሉም ሐዋርያት ከጌታ ጋር በነበራቸውየተማሪነት ቆይታ ከተረዷቸው ትምህርተ ሃይማኖት (ዶግማዎች) አንዱ ይህነው። ጌታምየሰውን ልጅ ሰዎች ማን እንደ ሆነ ይሉታል?” ብሎየጠየቃቸውና ቅዱስ ጴጥሮስ ትክክለኛውን መልስ ሲመልስ ማመስገኑ ይህንንሊያስተምራቸው ስለወደደ ነው። ፫፻ (ሠለስቱ ምዕት) በኒቅያ ጉባኤእምነታቸውን ሲመሰክሩ ካስቀመጡት ጸሎተ ሃይማኖት በፊት ይህ የቅዱስጴጥሮስ የእምነት አገላለጽ የጥንት ክርስቲያኖች ይህን እየመሰከሩ ይጠመቁነበር (በመንገድ ሲሄዱም ወደ ውኃ ደረሱ፤ ጃንደረባውም መልሶ፣ እነሆ ውኃመጠመቅን ምን ይከለክለኛል አለው። ፊልጶስም በፍጹም ልብህ ብታምንይገባሃል አለው። ጃንደረባውም መልሶኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔርልጅ እንደሆነ እኔ አምናለሁአለው . . .አጠመቀውምእንዲል /ሐዋ. ፰፥፳፮ - ፍጻሜ/ )

3. ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጌትነቱን በደብረ ታቦር ተራራ ከገለጠላቸው ሦስትሐዋርያት መካከል ቅዱስ ጴጥሮስ አንዱ ነው።ከስድስት ቀንም በኋላጌታችን ኢየሱስ ጴጥሮስን፣ ያዕቆብንና ወንድሙ ዮሐንስን ይዞ ለብቻቸውወደ ረጅም ተራራ አወጣቸው። መልኩም በፊታቸው ተለወጠ፥ ፊቱም እንደፀሐይ አበራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ። እነሆ፥ ሙሴና ኤልያስምከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው /ማቴ. ፲፯ - / ቅዱስ ጴጥሮስየጌታችንን ጌትነት ከተመለከተ በኋላ ከደስታው ብዛት የተነሣ ጌታችንንእንዲህ ብሎ ጠይቆት ነበር፤አቤቱ በዚህ መኖር ለእኛ መልካም ነው፤ብትወድስ፥ ሦስት ቤቶችን በዚህ እንሥራ፤ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴአንዱንም ለኤልያስ” /ማቴ.   ፲፯ - / ሙሴና ኤልያስ በደብረ ታቦርከጌታችን ጋራ መታየታቸው ለቅዱስ ጴጥሮስ እምነቱን የሚያረጋግጥለትናየሚያጸናለት ነገር ነው።ሰዎች እኔን ማን ይሉኛልብሎ በጠየቀ ጊዜኤልያስ ነው ወይም ከነብያት አንዱ (ሙሴ) ነውብለውት ነበርና የሙሴናኤልያስ ከጌታችን ጋር ሲነጋገሩ መታየት ጌታችን ሙሴ ወይም ኤልያስአለመሆኑን ያረጋግጣል። በተጨማሪም ለቅዱስ ጴጥሮስአንተ የሕያውእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ነህብሎ የመሰከረውን አብ ደግሞ በደመናሆኖየምወደው በእርሱ ደስ የሚለኝ ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙትማለቱየቅዱስ ጴጥሮስን ምስክርነት የሚያረጋግጥ ነው።

4. ጌታችንና ደቀ መዛሙርቱ ወደ ቅፍርናሆምም በመጡ ጊዜ የቤተ መቅደስግብር የሚቀበሉ ሰዎች ቅዱስ ጴጥሮስንመምህራችሁ ለቤተ መቅደስ ግብርይገብራል ወይስ አይገብርምየሚል ጥያቄ አቅርበውለት ነበር።ወደቅፍርናሆምም በመጡ ጊዜ ግብር የሚቀበሉ ሰዎች ወደ ጴጥሮስ መጥተውመምህራችሁ ሁለቱን ዲናር አይገብርምን? አሉት። እርሱም መልሶ አዎን(ይገብራል) አለእንዲል /ማቴ፲፯ ፳፬ - ፳፭/  ቅዱስ ጴጥሮስ ግብርተቀባዮች በጠየቁት ጊዜ ጌታችን የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነየመሰከረውንና ልጅ ደግሞ ከግብር ነጻ መሆኑን ባለማገናዘብአዎንይገብራልአላቸው። ጌታችንምአዎንማለቱን አውቆ እርሱ ከግብር ነጻመሆኑን በነገሥታት ልጆች ምሳሌ ካስረዳው በኋላ ነገር ግን እነርሱንላለማሰናከል በተአምራት ከዓሣ ሆድ ገንዘብ አስገኝቶ ለሁለታቸውምእንዲሰጥ አዘዘው።ወደ ቤትም በገባ ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ አስቀድሞ ስምዖንሆይ፥ ምን ትላለህ? የምድር ነገሥታት ቀረጥና ግብር ከማን ይቀበላሉ?ከልጆቻቸው ወይስ ከሌሎች? አለው። ጴጥሮስም፦ ከሌሎች ነው አለ፤ጌታችን ኢየሱስም አለው፤ እንኪያስ ልጆቻቸው ነጻ ናቸው። ነገር ግንእንዳያጉረመርሙ፥ ወደ ባሕር ሂድና መረብ ጣል፥ በመጀመሪያም የያዝከውንዓሣ ወስደህ አፉን ክፈት፤ በውስጡም ሰጣጢራ ታገኛለህ፤ ይከውም አራትድሪም ነው፤ እርሱንም ወስደህ ስለ እኔና ስለ አንተ ስጣቸው አለውእንዲልማቴ፲፯ ፥፳፭ ፍጻሜ/ እንዳያጉረመርሙ (እንዳናሰናክላቸው) ማለቱጌታችን የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ብሎ ለቤተመቅደስ ግብር ሳይገብር ቀርቶቢሆን ኖሮ አምላክነት ብቻ እንጂ ሰውነት የለውም ባሉ ነበርና ነው።

5. ቅዱስ ጴጥሮስ ትዳሩን፣ ቤቱን፣ ንብረቱን፣ ዘመዶቹን በአጠቃላይ ይህን ዓለምእርግፍ አድርጎ ትቶ ጌታችንን በመከተሉ ምን እንደሚያገኝ ጌታችንን በአንድወቅት ጠይቆት ነበር።ከዚህም በኋላ ጴጥሮስ መልሶ፥ ሁሉን ትተንተከተልንህ፣ እንግዲህ ምን እናገኛለን አለውእንዲል። ጌታችንም ሐዋርያትበጠቅላላ በፍጹም ልባቸው ዓለም በቃኝ ብለው እርሱን በመከተላቸውየሚያገኙትን ዋጋ ነገራቸው፤ እንዲህም አላቸው፡- “እውነት እላችኋለሁየተከተላችሁኝ እናንተ በዳግም ልደት የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን በተቀመጠጊዜ እናንተም በ፲፪ ዙፋን ትቀመጣላችሁ፤ በ፲፪ቱም ነገደ እሥራኤልትፈርዳላችሁ። ስለስሜም ቤትን፣ ወይም ወንድሞችን፣ ወይም እኅቶችን፣ወይም አባትን፣ ወይም እናትን፣ ወይም ሚስትን፣ ወይም ልጆችን፣ ወይምርስትን የተወ መቶ እጥፍ ዋጋ ያገኛል” /ማቴ. ፲፱ : ፳፯ - ፳፱/

6. መዝገበ ትሕትና የሆነው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀመዛሙርቱ ትሕትናን ሊያስተምራቸው ዝቅ ብሎ እግራቸውን ማጠብበጀመረ ጊዜ ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ሲደርስ ለጌታው ካለው አክብሮትና ፍቅርየተነሣ እንዲሁም እርሱ አምላክ ሲሆን ዝቅ ብሎ የእነርሱን እግር በማጠቡእጅግ ተደንቆበፍጹም አታጥበኝምአለ። ጌታችን ኢየሱስምእኔየምሠራውን አንተ ዛሬ አታውቅም፥ ኋላ ግን ታስተውለዋለህቢለውምአሁንም ቅዱስ ጴጥሮስ በጌታውና በአምላኩ እግሩን መታጠብ እጅግስለደነቀውና ስለከበደውመቼም ቢሆን አንተ እግሬን አታጥበኝምአለው።በዚህ ጊዜ ፈጽሞ እንቢ ማለቱን ባየ ጊዜእውነት እውነት እልሃለሁ እኔእግርህን ካላጠብሁህ፥ ከእኔ ጋር ዕድል ፋንታ የለህምብሎ መለሰለት።በዚህ ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስ ሁሉን ትቶ የተከተለውን ጌታ ከማጣት የሚበልጥምንም ነገር እንደሌለ ስለሚያውቅአቤቱ፥ እንኪያስ የምታጥበኝ እጆቼንናራሴንም እንጂ እግሮቼን ብቻ አይደለም አለው። ጌታችን ኢየሱስም፦ ፈጽሞየታጠበ ከእግሩ በቀር ሊታጠብ አያስፈልገውም፥ ሁለንተናው ንጹሕ ነውና፤እናንተማ ንጹሐን ናችሁ፥ ነገር ግን ሁላችሁ አይደላችሁም አለው።” /ዮሐ.፲፫ - ፲፩/

7. ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በካህናት አለቆችና በአይሁድ ሽማግሌዎች ተላልፎየሚሰጥበትና መከራ የሚቀበልበት ሰዓት ሲደርስ ይህንን መራራ እውነትለደቀ መዛሙርቱ ሲነገራቸው እጅግ ተረብሸው ነበር። ይባስ ብሎ ደግሞበመጨረሻው ሰዓት ሁሉም ደቀ መዛሙርት እንደሚክዱት በነገራቸው ጊዜቅዱስ ጴጥሮስሌሎች ቢክዱህ እንኳን እኔ በፍጹም አልክድህምአለው።ጌታችን እርሱ ባወቀ ዶሮ ሳየጮህ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ ቢለውም እርሱበፍጹምአለ። ነገር ግን አይሁድ ጌታችንን ይዘው መከራ ሲያጸኑበት አይቶእርሱን ያገኘ ያገኘኛል ብሎአንተ ከእርሱ ወገን ነህሲሉትበፍጹምአይደለሁምእያለ መማል ጀመረ። ወዲያው ዶሮ ሲጮክ ጌታ የተናገረውንቃል አስታውሶ በዚያችው ቃልአላበጀሁምበማለት በፍጹም ጸጸትማንባት ጀመረ(ንስሓ ገባ) /ማቴ. ፳፮ ፳፱ - ፍጻሜ/
 ቅዱስ ጴጥሮስ ለጌታችን ካለው ፍቅርና ቀረቤታ ታሪኩ በቅዱስ ወንጌል በስፋትተገልጿል፤ ሁሉንም ዘርዝሮ መጥቀስ ባይቻልም። ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታችን በእውነትከሙታን ተለይቶ መነሣቱን መቃብሩን በማየት ያረጋገጠ፣ ጌታችን ግልገሎቼንጠቦቶቼንና በጎቼን ጠብቅ ብሎ እንደሾመው እርሱም ልክ እንደጌታው ለበጎቹመልካም እረኛ በመሆን የታመነ፣ መንፈስ ቅዱስ ከወረደላቸው በኋላ በመንፈስ ቅዱስታድሶ በአንድ ጊዜ ሦስት ሺህ ነፍሳትን አሳምኖ ያጠመቀ፣ ብዙ ተአምራትን በጌታችንኃይል ያደረገ፣ የሐናንያንና የሰጲራን ድብቅ ሥራ በመንፈስ የመረመረ፣ በሰማርያበኢዮጴና በልዳ ዞሮ ወንጌልን ያስተማረ፣ በመጨሻም በሮማ ወንጌልን ሲሰብክበአደባባይ የቁልቁሊት ተሰቅሎ ፍጹም ጌታውን የመሰለ ታላቅ ሐዋርያ ነው።
 ቅዱስ ጴጥሮስ እየተዘዋወረ ሲያስተምር በወንጌል የወለዳቸውን ክርስቲያኖች ከልዩልዩ ፈተናዎች ለማጽናት ሲል ሁለት መልእክታትን ጽፏል። የመጀመሪያ መልእክቱንየጻፈው አይሁድ ለሚያሳድዷቸውና መከራ ለጸኑባቸው ከእስጢፋኖስ ሰማዕትነትበኋላ በስደት ለተበተኑ ክርስቲያኖች ነው። ሁለተኛውን መልእክቱን የጻፈበትምክንያት ደግሞ በወቅቱ የሮማ ግዛት መሪ የነበረው ኔሮን ቄሣር ክርስቲያኖች ሁሉእየተያዙ እንዲፈረድባቸው አዋጅ ነግሮ ነበርና በዚሁ ምክንያት ለተጨነቁ በእስያላሉ ክርስቲያኖች ነው። ከዚህም በተጨማሪ ሐሰተኞች መምህራን ተነሥተውበሐሰተኛ ትምህርታቸው ስላስጨነቋቸው ለማጽናት ጽፎላቸዋል።
 በታናሽ እስያ እየዞረ በቃልም በመጣፍም ካስተማረና አማንያንን በመከራ እንዲጸኑካደረገ በኋላ በስተመጨረሻ ወደ ሮሜ ገብቶ ያስተምር ጀመረ። በዚህ ጊዜ ኔሮንቄሣር አስይዞ አሳሰረውና በስቅላት እንዲቀጣ ተፈረደበት። ቅዱስ ጴጥሮስ በመስቀል ተሰቅሎ እንዲሞት መፈረዱን በሰማ ጊዜ ጌታችን፡- “በሸመገልህ ጊዜ እጆችህን ትዘረጋለህ፤ ሌላውም ያስታጥቅሃል ወደማትወደውም ይወስድሃልያለውን ቃል /ዮሐ.2118/ ትዝ አለውናአላውቀውም ብዬ መካዴን ሳያስብብኝ በዚህ ፍጹም ይቅርታ ያደርግልኛልበማለት እጅግ ደስ አለው፡፡ የሚሰቀልበትም ሰዓት በደረሰ ጊዜ ከግዞት ቤት አውጥተው ሲወስዱት፡- “ከጌታዬ ከኢየሱስ ክርስቶስ እኩል እንዳልሆን ራሴን ወደ ታች ዘቅዝቃችሁ ስቀሉኝብሎ ለመነ፡፡ እነርሱም እንደለመነው አድርገው ሰቅለው ገደሉት፡፡ የተሰቀለውም ሐምሌ አምስት ነው፡፡ ይህን ዕለት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በታላቅ የጸሎት ሥነ ሥርዓት ታከብረዋለች፡፡
በአጠቃላይ የቅዱስ ጴጥሮስ ሕይወት ታሪክ በአጭሩ ከላይ የቀረበው ነው፡፡ ከዚህ ቅዱስ አባት ሕይወት ብዙ የምንማረው አለ፡፡ አንድ ጊዜ ባጠፋው ጥፋት ሁል ጊዜ እየተጸጸተ የጌታውን ይቅር ባይነት ተስፋ ሳይቆርጥ በመረረ አንብዓ ንስሐው ይቅርታን ስላገኘ ለዘመኑ ተነሳሕያን (ንስሐ ለሚገቡ) ጥሩ ምሳሌ ነው፡፡ መዝሙረኛው ዳዊት መተላለፉን የቀረችለት፣ ኃጢአቱ የተከደነችለት፣ በደሉን የማይቆጠርለት ሰው ምስጉን ነው እንዳለ /መዝ.311-2/ እስከ ሞት ድረስ ፍቅሩን በመግለጽ ሰማዕትነትን በሮማ አደባባይ እስከተሰቀለበት ድረስ የአይሁድን ዱላ ፈርቶ በቀላሉ አላውቀውም ብሎ ለካደው አምላክ በቆራጥነትና በታማኝነት ቁልቁል እስከ መሰቀል የደረሰ ታላቅ ሐዋርያ ነው፡፡
ጸሎቱና በረከቱ በእኛ በሕዝበ ክርስቲያን ላይ አድሮ ይኑር አሜን፡፡

No comments:

Post a Comment