በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ባለፈው ዝግጅታችን ስለቅዱሳን ሐዋርያት አጠቃላይ መግቢያ አቅርበን በቀጣይነትደግሞ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የእያንዳንዱን ሐዋርያ የተጋድሎ ሕይወት በዝርዝርእንደምናቀርብ ቃል ገብተን ነበር (የባለፈውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ-http://mekrez.blogspot.com/2012/09/blog-post_12.html)። በመሆኑም ለዛሬየሐዋርያት አለቃ የሆነውን የሐዋርያው የቅዱስ ጴጥሮስን ሕይወትና ተጋድሎ እነሆብለናል መልካም ንባብ።
ቅዱስ ጴጥሮስ
የተወለደው በገሊላ ባሕር ዳርቻ ( የገሊላ ባሕር ፫ ስያሜዎችአሉት፡- (፩) የገሊላ ባሕር
(በገሊላ አውራጃ ስለሚገኝ)፣ በዙሪያው ባሉ ጌንሴሬጥናጥብርያዶስ በሚባሉ ከተሞች ስም ደግሞ (፪) ባሕረ ጌንሴሬጥ እና (፫) ባሕረጥብርያዶስ ይባላል)
ባለች ቤተሳይዳ በተባለች ከተማ ውስጥ ነው የአባቱ ስም ዮናሲሆን ትውልዱም ከነገደ ሮቤል ነው። እናቱ ደግሞ ከነገደ ስምዖን ወገን የሆነችነበረች። በመሆኑም እንደ ኦሪት ሥርዐት ስም ሲያወጡለት በእናቱ ነገድ ስምስምዖን ብለውታል። አባቱ ዮና የያዕቆብና የዮሐንስ አባት ከሆነው ከዘብዴዎስ ጋርየሥራ ባልንጀራ ሲሆን የሁለቱም ሥራቸው ዓሣ እያጠመዱ መሸጥ ነበር። እድሜው፭ ዓመት ሲሆን ኦሪትን እየተማረ እንዲያድግ በአቅራቢያቸው ወዳለ ወደቅፍርናሆም ምኩራብ ሰደዱት። ቅዱስ ጴጥሮስ በቅፍርናሆም እየተማረ ካደገ በኋላበዚያው ቤት ሠርቶ ኮንኮርድያ (ጴርጴቱዋ) የምትባል ሚስት አግብቶ እንደ አባቱዓሣ እያጠመደ በመሸጥ መኖር ጀመረ።







