ቤተ ክርስቲያናችን ከምታከብራቸው ዓበይት በዓላት መካከል አንዱ በዓለ ጰራቅሊጦስ ነው፡፡ ይህ በዓል ጌታችን በሚያርግበት ጊዜ ደቀመዛሙርቱን
‹አንትሙሰ
ንበሩ ሀገረ ኢየሩሳሌም እሰከ ትለብሱ ኃይለ እም አርያም › ሉቃ 24፤49
ብሏቸው አርጎ ነበር፡፡ ተናግሮ የማያስቀር ነውና ባረገ በ10ኛው በተነሣ በ50ኛው ቀን ጰራቅሊጦስን ሰዶላቸዋል ፡፡
ጰራቅሊጦስ ማለት ፡-
1.
ናዛዚ(አጽናኝ)
ማለት ነው ከመንፈስ ቅዱስ ሥራዎች አንዱ ያዘኑትን የተጨነቁትን በተለያየ ነገር ውስጥ ገብተው ግራ የተጋቡትን ሁለ ሰለሚያጽናና ናዛዚ ይባላል ፡፡
2.
ከሣቲ (ምስጢር
ገላጭ) ማለት ነው የተደበቀውን የሚገልጥ የረቀቀውን የሚያገዝፍ የተሰወረውን የሚያሳይ በመሆኑ ከሣቲ ( ምስጢር ገላጭ) ይባላል ፡፡
3.
መጽንኢ (የሚያጸና)
በተለያየ ሁኔታ ውስጥ ገብተው የሚባዝኑት ለመውደቅ የተፍገመገሙትን እንዳይወድቁ የሚደግፍና የሚያጸና በመሆኑ መጽንኢ (የሚያጸና) ይባላል ፡፡
4.
መንጽሂ (የሚያነጻ)
ማለት ነው በኃጢአት የወደቁትን ከኃጢአታቸው የሚያነጻቸው ነውና መንጽሂ (የሚያነጻ) ይባላል ፡፡
5.
መሠተሰርየ (ይቅር
ባይ )ማለት ነው በኃጢአት የወደቁትን የበደሉትን ተጸጽተው ንሰሃ ሲገቡ ይቅር የሚል በመሆኑ መሠተሰርይ ይቅር ባይ ይባላል ፡፡
6.
መስተፈሥሔ (ደስታን
የሚሰጥ ) ማለት ነው የተጨነቁት፤ ያዘኑትን፤ያለቀሱትን እንባቸውን የሚያብስና ደስታን የሚሰጥ በመሆኑ መስተፈሥሔ (ደስታን የሚሰጥ) ይባላል ፡፡
በአጠቃላይ ጰራቅሊጦስ ማለት መንፈሰ ጽድቅ ፤መንፈሰ ሕይወት ፤ባሕርያዊ እስትንፋስ ፤ አካላዊ ሕይወት
፤አካላዊ እስትንፋስ ማለት ነው፡፡