Thursday, February 23, 2012

ኪዳነ ምሕረት


የምሕረት እናታችን ኪዳነ ምሕረት

ኪዳን የሚለው ቃል ‹‹ቃል›› ከሚለው ጋር እየተዛረፈ በብሉይ ኪዳን ለ280 ጊዜ ያህል ሲጠቀስ በአዲሰ ኪዳን ደግሞ ከ32 ጊዜ በላይ ተጠቅሷል፡፡ ‹‹ኪዳን›› ቃሉ ‹‹ተካየደ›› ተማማለ፣ ቃል ተገባባ ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ነው፡፡ ‹‹ምሕረት›› የሚለው ቃል ደግሞ ማብራሪያ ሳያሻው ምሥጢሩ ከነዘይቤው ከግእዝ የተወረሰ ነው፡፡ ስለዚህ ኪዳነ ምሕረት ማለት የምሕረት፣ የይቅርታ ውል፣ ስምምነት፣ መሐላ ማለት ነው፡፡ ኪዳን ከተራ ውሎችና ስምምነቶች የበለጠ ጽኑና ቀዋሚ ነው፡፡ ከፍ ያለ ክብደትም አለው፡፡

‹‹ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አድርጋለሁ›› ተብሎ በዳዊት መዝሙር እንደተጻፈ እግዚአብሔር ከመረጣቸው ቅዱሳኑ ሁሉ ጋር ቃል ኪዳን አድርጓል፡፡ ወደፊትም ያደርጋል፡፡ (መዝ88.3) ቃል ኪዳኑም የምሕረት ቃል ኪዳን ነው፡፡

Monday, February 13, 2012

ዐቢይ ጾም


ጌታ በሰይጣን እንደተፈተነ
በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ባሕልና ትውፊት  እና ሥርዓት መሠረት በዘንድሮው ዓመት በመጪው ሰኞ የካቲት ፲፪ ቀን ፳፻፬ .. ( February 20, 2012 ) የሚጀመረው የጾም ወራት ከሰባቱ አጽዋማት አንዱና ዋነኛው፣ ጌታ ከተጠመቀ በኋላ የጾመው የአርባ ቀን ጾም ነው፡፡ ምእመናን ጌታቸው ያደረገውን ምሳሌ ተከትለው ይጾሙታል፡፡

   ይህ ታላቅ የሆነው የጾማችን ወራት በተለያየ ስያሜ  ይጠራል፡፡
1. ዐቢይ ጾም ይባላል፡፡

ሌሎች አጽዋማት ከቅዱሳን አበው የወረስናቸው የኑሮአቸው ፍሬዎች (ዕብ.137) ሲሆኑ ይኼኛው ግን በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የተመሠረተ በመሆኑ ዐቢይ (ታላቅ) ይባላል፡፡ የጌታ ጾም ስለሆነ ታላላቅ የሰይጣን ፈተናዎች (አርእስተ ኃጣውእ) ድል የተነሡበት፣ ድል የሚነሡበት ጾም ስለሆነም ዐቢይ ጾም ይባላል፡፡ 

Monday, February 6, 2012

ጾመ ነነዌ

ዲ.ዮናታን ጌታቸው
ነነዌ  ከሰባቱ ዐበይት አጽዋማት መካከል አንዱ ነው። ከ አጽዋማቱ መካከል አንዱም ብቻ ሳይሆን ለዓቢይ ጾም ማዘጋጃም ነው።

እንኳን ለጾመ ነነዌ አደረሰዎት
 ነነዌ በጥንት ጊዜ የነበረች   በጤግሮስ ወንዝ ዳር በናምሩድ የተመሰረተች ከተማ ናት:: ዘፍ 10፥11-12 የከተማው ቅጥር ርዝመት ዐሥራ ሁለት ኪ.ሜ ያህል ነው:: ሰናክሬም በወስጧ ብዙ ሕንጻዎችን ሠርቷል:: ኋላም በባቢሎን መንግሥት ፈርሳለች፡፡

እግዚአብሔር ነብዩ ዮናስን ወደ ነነዌ ምድር በኃጢአታቸው ምክንያት ሊያመጣው ካሰበው የእሳት ዝናም እንዲትርፉ ቢልከው የ እግዚአብሔርን ቸርነት ስለሚያውቀው ቸ ርነትህ ከልክላህ ሳታጠፋቸው ብትቀር እኔ የሐሰት ነቢይ እባል የለምን? ብሎ ሰግቶ ወደ ተርሴስ  ሃገር  ከነጋዴዎች ጋር ተሳፈረ። እግዚአብሔርም ታላቅ ማዕበልን አስነሳ በመርከቧ ያሉ ሰዎችም እርስ በራሳቸው ዕጣን ተጣጥለው በዮናስ ላይ ወደቀ። እርሱም ያደረገውን ሰለሚያውቅ ሌሎቹ በውሰጥ ያሉት እንዳይጣልብዙ ጥረት ቢያደርጉም የግድ መጣል ስለ ነበረበት ወደ ባሕር ተጣለ።  እግዚአብሔርም ታላቅ ዓሣ አንበሪን አዘጋጅቶ በከርሠ ዓሣ አንበሪ ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት ቆይቶ  በሦስተኛው ቀን  በአንጻረ  ነነዌ  ተፍቶታል። በግድም ቢሆን ስለ ሚመጣባቸው መዓት አስተምሯል። ትንቢተ ዮናስ ምዕራፍ 1 እና 2። ነብዩ  ዮናስ ለመጀመርያ ጊዜ ወደ አሕዛብ ሀገር የተላከ ነቢይ ነው።