ይህን ያውቁ ኖሯል?


4 comments:

 1. ውዳሴ ማርያም በ መፅሐፍ ቅዱስ።

  ውዳሴ ማርያም በ መፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለ አንጂ ደራሽ ድርሰት አንዳልሆነ ማወቅ ተገቢ ነው። በመንፈስ ቅዱስ የተቃኘው ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬም ፃፈልን። አንዳንዶቻችን ውዳሴ ማርያምን በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ በብሉይ ኪዳንም ሆነ በአዲስ ኪዳን አንዳለ ያላወቅን ካለን ልብ ልንል ይገባል። በብሉይ ኪዳንም ሆነ በአዲስ ኪዳንም ቅዱሳን ነቢያት አና ቅዱሳን መላክት ለአመበታችን ውዳሴ አቅርበዋል

  ከክርስቶስ ልደት በፊት ከዘጠኝ መቶ ዓመት በፊት የኖረው ቅዱስ ዳዊት ለአመበታችን ውዳሴ ፅፏል

  ፩/ መዝ. 44 ፥ 10 '' ልጄ ሆይ ስሚ፣ ጆሮሽንም አዘንብዬ ወገንሽን ያባትሽንም ቤት አርሺ ንጉስ ውበትሽን ወዷልና''

  ፪/ ንጉስ ሰለሞን ለአመበታችን ውዳሴ ፅፏል በመሃልየ ሶሎሞን ፫።''ወዳጄ ሆይ ሁለንተናሽ ውብ ነው፣ ነውርም የለብሽም ሙሽራዬ ሆይ ከሊባኖስ ነይ''

  ፫/ ቅድስት ኤልሳቤት አመበታችንን አወድሳታለች-

  ሉቃስ ወንጌል ፩ ፥ ፬፬ '' በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ ሞላባት አና በታላቅ ድምፅ ጮሃ አንዲህ አለች ''ከሴቶች ተለይተሽ አንቺ የተባረክሽ ነሽ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው ፣ የጌታዬ አናት ወደ አኔ ትመጣ ዘንድ አኔ ምንድነኝ''

  ፬/ መላክት ለአመበታችን ውዳሴ አቅርበዋል

  ሉቃስ ፩ ፥ ፪፰ ''መላኩም ወደርሷ ቀርቦ ፀጋ የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ አግዝያብሔር ካንቺ ጋር ነው ከሴቶች ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ''

  ፭/ ምመናን አመስግነዋታል

  ሉቃስ ፩፩ ፥ ፪፯ '' አንተን ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን የተሸከመች ማህፀን ብፅይት ናት፣ የድንግልና ወተትን አያጠቡ ያሳደጉህ ጡቶችም ንዑዳን ክብራን ናቸው''

  በብሉይ ኪዳንም ሆነ በአዲስ ኪዳንም ቅዱሳን ነቢያት አና ቅዱሳን መላክት ለአመበታችን ውዳሴ አቅርበዋል። በሁአላ መፅሐፍ ቅዱሱን መሰረት አርጎ የአምላክን ሰው መሆን፣የአመበታችንን የአምላክ አናትነት ከመፅሐፍ ቅዱሱ ጋር አያመሳጠሩ ቅዱስ ኤፍሬም ውዳሴ ማርያምን ቅዱስ ያሬድ ደግሞ አንቀፀ ብርሃንን ፃፉልን።

  አናም ውዳሴ ማርያም፣ አንቀፀ ብርሃን መልካ መልኮቻችን መፅሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት ያላቸው መሆኑን ማወቅ አና ማሳወቅ ከተዋህዶ ልጆች ይጠበቃል።

  ReplyDelete
 2. በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
  እንኳን ለቅድስት ሥላሴ መታሰቢያ በዓላቸው በሰላም አደረሰን፤ እንዲሁ ደግሞ ለመጪው ወርና ብዙ ዘመናት በሰላም ያድርሰን፡፡
  ለህታዌክሙ፡-
  አብ፡ወልድ፡መንፈስ፡ቅዱስ፡ሆይ፡ የፍጥረት ሁሉ ስነ ባህርይ ፈጥሮ በበላይነት ለሚገዛ መለኮታዊ ሥነ አእምሮ ሰላምታ ይገባል፡፡
  ሥሉስ ቅዱስ ሆይ፡-
  ... በተመኘሁ ጊዜ የክብር ሦስትነታችሁን ለማግኘት ተመራምሮ አንድነትን ከሦስትነት ሳይቀላቅል የመለኮት አንድነት በዘላለማዊት ሕልውና አምናለሁ፡፡
  ለዝክረ ስመክሙ፡- አብ፡ወልድ፡መንፈስ፡ቅዱስ፡ሆይ፡-
  ከሦስትነት ዝቅ ወይም ከፍ ለማይል የስም አጠራራችሁ ሰላምታ ይገባል፡፡
  ሥሉስ ቅዱስ ሆይ፡-
  በሦስትነት ጸንቶ ለሚኖር የባህርይ አምላክነታችሁ መለኮታዊ እጅ ከተከለው፡ ተክለ ጽድቅ ፍሬያችሁከወይን ዘለላ ቸርነታችሁ ትመግቡኝ ዘንድ ደጅ እጠናለሁ እኔ አገልጋያችሁ (ከመልከአ ሥላሴ የተወሰደ)
  የዓለም ገዢ ሥሉስ ቅዱስ ሆይ፡-
  በወዳጃችሁ በአርሃም እንደገባችሁ ከእናንተ ዘንድ የሚሰጠውን ሰማዕትነት በአክሊል እቀዳጅ ዘንድ ተድላ ደስታ ካለበት ገነት አግቡኝ፡፡ ሃጢአቴን በይቅርታ ቃል ደምስሳችሁነፍሴን ከሚቃወሟት አጋንንት አድኗት፡፡
  አብ፡ወልድ፡መንፈስ፡ቅዱስ፡ሆይ፡-
  በእውነት ስማችሁን እጠራ ዘንድ ከወደኩበት አንሱኝ ከሩቅ ጥቀሱኝ ከቀትር ጋኔን ከድንገተኛ መጋኛ ትጠብቁኝ ዘንድ እማጸናለሁ፡፡
  አብ፡ወልድ፡መንፈስ፡ቅዱስ፡ሆይ፡-የምስጋና፡ፍሬ፡እንዳፈራና፤ከአንደበቴም፡የጸሎት፡እሸት፡አበረክትላችሁ፡ዘንድ፡በልቡናዬ፡እርሻ፡ላይ፡መልካሙን፡ፍሬ፡ትዘሩ፡ዘንድ፡እማፀናለው፡፡ (ሰይፈ ሥላሴ ዘዘወትር)

  “ወንድሞቻችን እኛስ እንዲህ እናምናለን ያልተወለደ እግዚአብሔር አብ በተለየ አካሉ አንድ ነው፤የተወለደ እግዚአብሔር ወልድ ዋሕድ ኢየሱስ ክርስቶስም በተለየ አካሉ አንድ ነው፡፡ በወደደው የሚያድር የአብ የወልድ እስትንፋስ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስም በተለየ አካሉ አንድ ነው፡፡አብ አልተወለደም ዓለም ሁሉ ሳይፈጠር ወልድን የወለደ ነው እንጂ ወልድም ዓለም ሁሉ ሳይፈጠር ከእግዚአብሔር አብ ተወለደ፤መንፈስ ቅዱስም ዓለም ሁሉ ሳይፈጠር ከእግዚአብሔር አብ ሠረጸ፡፡ (ሃይማኖተ አበው ዘአትናቲዎስ ገጽ ፶፭፡፡)
  “ሰናቋርጥ የሦስቱን ምስጋና አንድነት እንናገራለን ፍጹም አሸናፊ አንድ አምላክ እግዚአብሔር አብ፤ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ተብለህ የምትመሰገነው ምስጋናህ በሰማይ በምድር ምሉ ነው፡፡ ( ሃይማኖተ አበው ዘጎርጎርዮስ ገጽ ፩፻፲፪ ፡፡)
  “አብ በአካሉ በገጹ በመልኩ ያለ ነውና ወልድም እንዲሁ በአካሉ በገጹ በመልኩ ያለ ነውና መንፈስ ቅዱስም እንዲሁ በአካሉ በገጹ በመልኩ ያለ ነውና እንደሰውም አይወሰኑም አምላክነት ያለው አካላት ናቸውና፡፡ በአካል ሦስት በባሕርይ አንድ ብሎ ይህን ሃይማኖት የማያምን አንዲህ እኛ እንደወሰንነው አድርጎ ሃይማኖቱን የማይጽፍ ቢኖር ሐዋርያት ያስተማሯት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታወግዘዋለች” ( ሃይማኖተ አበው ዘአትናቴዎስ ገጽ ፹፩ ፦ም.፳፮ ፡፡ )

  ReplyDelete
 3. አባ መቃርዮስ
  በአንድ ወቅት አባ መቃርዮስ ይህንን ታሪክ ተናግሮ ነበር። ወጣት ሆኘ በአንዲት በዓት ውስጥ ስኖር መንደሩ ጸሐፊ ሊያደርጉኝ ፍለጉ። ይህንን ክብር መቀበል ስላልፈለኩ ሸሽቼወደ ሌላ መንደር ገባሁ። ሸሽቼ ስሔድም አንድ ሰው አብሮኝ ነበረ። ያም ሰው እኔ በእጄየምሰራውን እየሸጠልኝ ያገለግለኝ ነበር። በዚህ መሐል በዚያ መንደር የምትኖር አንዲትድንግል የነበረች ሴት ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ አርግዛ ተገኘች። ማርገዟም በታወቀ ጊዜከማን እንደጸነሰች ቤተሰቦቿ አጥብቀው ጠየቋት። እሷም የደፈረኝ እና የጸነስኩትም ከዛመናኝ ሰው ጋር ነ ብላ ነገረቻቸው። ቢዚህን ጊዜ መንደርተኞችም ሲሰሙ በፍጥነትመጥተው ያዙኝ። በጣም ጥቁር የመሰለ ማሰሮ እና ሌሎችንም የወዳደቁ ነገሮች በአንገቴዙሪያ አጠለቁብኝ ከዛም ወደ መንደሮችና አደባባዮች እያዳፉ ወሰዱኝ። በጣምምአብዝተው ይደበድቡኛል። ደግሞም « ይህ መነኩሴ ልጃችንን አበላሸ፤ ያዙት፤ በሉትእያሉ ይቀጠቅጡኛል» ብዙም ክፉ ቃላትን ይናገሩ ነበር።

  እስከ ሞት ድረስ ደበደቡኝ። ከሽማግሌዎች አንዱ ወደ እኔ ቀረበና « ምን እያደረጋችሁነው ምንስ መስራታችሁ ይህን እንግዳ መነኩሴ መከራውን የምታሳዩት ደግሞስ እስከሞት ድረስ እንደዚህ የምትደበድቡት» ምክኒያታችሁስ ምንድን ነው ብሎ ጠየቃቸው። ያእኔን ያገለግለኝ የነበረ ሰው በሃፍረት ስሜት ውስጥ ሆኖ በኋላየ ይከተለኝ ነበር። እሱምእኔን እንደሚያገለግለኝ ያውቁ የነበሩ ሰዎች እርሱን ይሰድቡት ነበር። « ተመልከትይህንን አብዝተህ ታምነውና ታገለግለው የነበረው መነኩሴ እንደዚህ አሳፋሪ፤ ዘግናኝ እናአስነዋሪ ስራ በንጹህ ልጃችን ያደረገውን ስራ? አያሳፍርም? ምን እንደሰራ አየህ? ይሉትነበር። የልጅቱም ወላጆች « ልጃችንን ለመንከባከብ ቃል እስኪገባ ድረስ እንዳትለቁት»ብለው ትዕዛዝ አስተላለፉ። እኔም ያንን ትዕዛዝ ሙሉ በሙሉ እንደምፈጽምላቸው ቃልከገባሁላቸው በኋላ ወደ ቤቴ እንድሄድ ፈቀዱልኝ። እኔም ከዛ መከራ፤ ስቃይና እንግልትእንደተላቀኩ ባየሁ ጊዜ አምላኬን አመስግኜ ወደ በኣቴ ተመለስኩ።
  ከዚያምየሚያገለግለኝን ሰው « ያለኝን ቅርጫቶች ሽጥና ለዚያች ሴት ስጥልኝ» አልኩት እርሱምእንዳልኩት አደረገ። ለራሴም መቃርዮስ ሆይ ለራስህ ሚስት አግንተሃል፤ እርሷንመንከባከብ ትችል ዘንድ ካለፈው የተሻለ ስራ መስራት አለብህ ብየ ለራሴ ነገርኩት።ከዚያም ሌትና ቀን መስራት ጀመርኩ። ያፈራሁትንም ገንዘብ ለልጅቷ እየላኩ መርዳትጀመርኩ። ለብዙ ጊዜ እንደዚህ እያደረኩ መውለጃዋ ጊዜ እስኪደርስ ድረስ እረዳት ነበር።የመውለጃዋ ቀን በደረሰ ጊዜ ምጡ በዛባት ለብዙ ቀናት ብታምጥም መውለድ ግንአልቻለችም ነበር። « መንደርተኞችም ተሰባሰቡ፤ ተጨነቁ ደግሞም እርስ በእርሳቸውይነጋገሩ ጀመር ምንድን ነው ችግሩ እያሉ። የልጅቷ ምጥም እየበዛ፤ እየተሰቃየችበመጣች ጊዜ ምንድን ነው ችግሩ? ብለው እሷን ጠየቋት። እሷም « ምክኒያቱንአውቄዋለሁ፤ ያንን መናኝ ባልፈጸመው ድርጊት ስለ ወነጀልኩት ነው የጸነስኩት ከሱአልነበረም፤ የጸነስኩት ከእገሌ ነው ብላ እውነቱን ከእንባ ጋር ነገረቻቸው።
  በዚህን ጊዜ ያያገለግለኝ የነበረው ሰው በጣም ከመደሰቱ የተነሳ እይሮጠ ወደ እኔ ፈጥኖ መጣናየምስራች ብሎ ሁሉን ነገር ገልጦ ነገረኝ። ያች ሴት የጸነስኩት ከመነኩሴው አይደለምእስክትልና እውነቱን እስክትናገር ድረስ መውለድ አልቻለችም ስለዚህ ያ እንደዚያሲያሰቃዩህ የነበሩት መንደርተኞች በሙሉ መጥተው ይቅርታ ሊጠይቁህ በዝግጅት ላይናቸው አለኝ። ነገር ግን ይህንን ስሰማ ሕዝቡ ስለ እኔ መልካም በማውራት ነብሴንበውዳሴ ያዝሏታል ብየ በመፍራት ሸሸሁ ወደ ሌላ ገዳምም ሄድኩ። ስለዚህ እኛ ከዚህምን እንማራለን? ሰውን በሃሰት ከመክሰስ፤ ከመውንጀል መታቀብ ይኖርብናል። ለዚህምእግዚአብሔር አምላካችን ይርዳን።
  የአባታችን የመቃርዮስ በረከታቸው እና ረድኤታቸውአይለየን አሜን።

  ReplyDelete