በጎርፍ ምክንያት የሚሸረሸር መሬት፦ ዝም ካልነው መሬቱ ተሸርሽሮ፦ የመሬቱ ገጽታ ተቀይሮ ፤ ከጥቅም ውጪ ሆኖ ይቀይራል።
የመሬቱን መሸርሸር ለማቆም ግድብ መሥራት የግ ይላል። እኛ አሁን መነጋገርና መሥራት ያለብንም መገደብ ያልቻልነው ለምንድን ነው?
የት እና እንዴት ነው የምንገድበው? በሚሉት ጉዳዮች ላይ ነው። ከዚያም በኋላ በሌሎች ቦታዎች ላይ ተመሳሳይ ችግር እንዳይፈጠር
በዕቅድ መሥራት እንችላለን። የአጭርና ረዥም ጊዜ ዕቅድ ንድፍ ይዘን የምንጓዝ ከሆነ እንደየአካባቢውና እንደየሁኔታው ለሚፈጠሩ ችግሮች
መሠረታዊና ለቦታው የሚስማማ የአሠራር ዘዴዎችን መዘርጋት ቀላል ይሆናል።
እንግዲህ በዚህ ዘመን ያለነው ክርስቲያኖች ከዚህ የምንማረው ምንድን ነው? ከእኛስ የሚጠበቀው እስከምን ድረስ ነው? እስከሞት
ድረስ መታመን እንችላለን ወይ? ቤተክርስቲያን እየደረሰባት ያለው ፈተና
እንዴት ሊበዛ ቻለ? መፍትሔውስ ምንድን ነው? በኢትዮጵያ፦ በሰሜን አሜሪካ እና በሌሎች ክፍላተ ዓለማት ብዙ ማኅበራት
አሉ፦ በኅብረት መሥራት አይቻልም ወይ? ቤተክርስቲያንን በየጊዜው እየከበባት ያለውን የጥፋት ዘመቻ መግታት የሚቻለው እንዴት ነው?
ከሃይማኖታችን ኃላፊነት ግዴታ አንጻር ብዙ ያልሠራነው እኛ ወይስ የሃይማኖት መሪዎች? ዛሬ በየገዳማቱ ላይ በተደጋጋሚ እየደረሱ
ላሉት ጥቃቶች ተጠያቂው ማን ነው? መፍትሔዎቻቸውስ? ቤተክርስቲያንን አብዝቶ እየጎዳት ያለው የውስት ወይስ ከውጪ የሚመጣ ፈተና?
የቤተክርስቲያን ጠላቶች ዓላማ ግልፅና የታወቀ ሲሆን መግታት ያልቻልንበት
በምን ምክንያት ነው? በሰከነ ልብ፦ በበሰለ አዕምሮ ፦ በለዘበ አንደበት፦
የቤተክርስቲያንን ጥቅም ባማከለ ሁኔታ እስኪ እንነጋገር፦ እንመካከር፦ እንጸልይ። በነገር ሁሉ እግዚአብሔር ማስተዋሉን ይስጠን!
አሜን! ፪ ጢሞ ፪፡፯