ምንኵስና በኢትዮጵያ
ከ4ኛው መ/ክ/ዘ በፊት
ሥርዓተ ምንኵስና ወደ ሀገራችን የገባው በኢትዮጵያ በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ በአባ ጳኩሚስ ዘመን ቢሆንም የብሕትውና ኑሮ ግን በሀገራችን ከዚያም ቀድሞ እንደነበረ የሚጠቁሙ አንዳንድ መረጃዎች አሉ፡፡
አባ አሞንዮስ፡- ሥርዓተ ምንኵስና ወደ ኢትዮጵያ ከመግባቱ በፊት አሞንዮስ የተባሉ ባሕታዊ በተንቤን ቆላ ደብረ አንሣ በተባለው በረሃ በጾም በጸሎት ተወስነው ይኖሩ ነበር፡፡
አባ ዮሐኒ፡- በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን መግቢያ ላይ በትግራይ ተንቤን አውራጃ በሀገረ ሰላም ቀበሌ ተወለዱ፡፡ በዚያን ዘመን ሥርዓተ ምንኵስና ወደ ኢትዮጵያ ባይገባም አበው በምናኔ በበረሃ ይኖሩ ነበር፡፡ የአባ ዮሐኒ ቤተሰቦች ድሆች ስለነበሩ አባ አሞንዮስ ወስደው አሳደጓቸው፡፡ ካደጉ በኋላም ከአባ አሞንዮስ ተለይተው ወደ በረሃ ለብቻቸው በመውረድ በተጋድሎ ሲኖሩ ከቆዩ በኋላ በተወለዱ በ3ዐ ዓመታቸው ኀዳር 5 ቀን እግዚአብሔር ወደ ብሔረ ሕያዋን በመላእክት እጅ እንደወሰዳቸው ገድለ አባ ዮሐኒ ይገልጣል፡፡
ሥርዓተ ምንኵስና በኢትዮጵያ ለመስፋፋት የበቃው በሁለት ዓይነት መንገድ ነው፡፡
- ከውጭ ወደ ሀገራችን በገቡ ቅዱሳን
- በኢትዮጵያውያን ቅዱሳን
ወደ ሀገራችን የገቡ ቅዱሳን፡
ከመካከለኛው ምሥራቅ፣ ከታናሸ እስያና ከሮማ ግዛት ወደ ሀገራችን በልዩ ልዩ ምክንያት ገብተው ሥርዓተ ምንኵስናን ያስፋፉ ገዳማትን የገደሙ አበው አያሌ ሲሆኑ ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡
አባ ሊባኖስ፡-
በቁስጥንጥንያ አጠገብ ሩም በተባለች ቀበሌ ተወለደ፡፡ በልጅነቱ በዲቁና ሲያገለግል ቆይቶ ወደ ግብፅ በመምጣት ሥርዓተ ምንኵስና ተፈጸመለት፡፡ ወደ እስክንድርያ በመጓዝም እስከ ቁምስና ማዕረግ የደረሰ አባት ነው፡፡ በ486 ዓ.ም. ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት 8ዐ ዋሻዎች አንፆ ሥርዓተ ምንኵስናን አስፋፍቶ በዐፄ ገብረ መስቀል ዘመነ መንግሥት ጥር 3 ዐርፏል፡፡
ተስዐቱ ቅዱሳን
ተስዐቱ ቅዱሳን
ተሰዐቱ ቅዱሳን |
ስም
|
ገዳም
|
የዕረፍት ቀን
|
ሀገራቸው
|
አባ አሴፍ |
ብኀዛን (አህስአ)
|
መጋቢት 11
|
ቂሣርያ
|
አባ አረጋዊ
|
ደብረ ዳሞ
|
ጥቅምት 14
|
ሮም
|
አባ አፍጼ
|
የሃ/ዬሐ
|
ግንቦት 12
|
እስያ
|
አባ ሊቃኖስ
|
ደብረ ቆናጽል
|
ኀዳር 21
|
ቁስጥንጥንያ
|
አባ ገሪማ
|
መዱራ
|
ሰኔ 29
|
ሮም
|
አባ ጉባ
|
ገርዓልታ
|
ግንቦት 29
|
ኪልቂያ
|
አባ ይምዓታ
|
ገርርዓልታ
|
ጥቅምት 23
|
ቆሲያ
|
አባ ጰንጠሌዎን
|
አኵስም (አጠገብ)
|
ጥቅምት 6
|
ሮም
|
አባ ጽሕማ
|
ጼዴንያ
|
ጥር 16
|
አንጾኪያ
|
የትውልድ ሀገራቸው ፍልስጥኤም ሲሆን ወደ ኢትዮጵያ የገቡት በ11ዐዐ ዓ.ም. ነው፡፡ አባ ዮሐንስ በተለይ ከአፋር ክልል ደብረ አዘሎ፣ ደብረ ደንኖ፣ ደብረ ፀገ፣ ደብረ ገሮ፣ ደብረ አሳራ በተባሉ ሥፍራዎች ሥርዓተ ምንኵስናን አስፋፍተዋል፡፡ በመጨረሻም በለሳ በረሃ ወርደው ጐንድ ገዳምን በመመሥረት ሐምሌ 29 ቀን በተወለዱ በ5ዐዐ ዓመታቸው በ15ዐዐ ዓ.ም. ዐርፈዋል፡፡
ጻድቃን
ተሰዐቱ ቅዱሳን ወደ ኢትዮጵያ ከመምጣታቸው በፊት በግልና በኀብረት እየሆኑ አያሌ መነኰሳት ወደ ሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ገብተው ነበር፡፡ እነዚህም ቅዱሳን (ጻድቃን) እየተባሉ ሲሆን በቅርቡ መጽሐፈ ገድላቸው እስከ ተገኘበት ጊዜ ድረስ ስለነርሱ የሚታወቀው እጅግ ጥቂት ነበር፡፡ እነርሱም በኤርትራ ቆላማው ሥፍራ ሥርዓተ ምንኵስናን ያስፋፉ መሆናቸው ታውቋል፡፡
አርባ ሐራ፡-
አቡነ ሐራ የተባሉት ቅዱስ በዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከግብፅ ወደ ኢትዮጵያ በመግባት በአኵስም ከቆዩ በኋላ አያሌ መጻሕፍት እና ንዋያተ ቅድሳት ይዘው ወደ መንዝ ማማ ምድር በመምጣት በዋሻ ውስጥ ተቀመጡ፡፡ የዮዲት ዘመን ካለፈ በኋላ ደግሞ 4ዐ ቅዱሳን ከግብፅ ከገዳመ አስቄጥስ መጥተው ከአቡነ ሐራ ጋር 4 ሰዓት የሚያስኬድ ዋሻ ፈልፍለው ማኀበረ መነኰሳት አቁመው መኖር ጀመሩ፡፡
ከዚህም መካከል 2ዐዎቹ ዞረው ሲያስተምሩ 2ዐዎቹ ደግሞ የተግባር ቤቱን ሥራ ያከናወኑ ነበር፡፡
በአካባቢውም ትምህርተ ወንጌልንና ሥርዓተ ምንኵስናን ካስፋፉ በኋላ አስቀድመው 4ዐው ቅዱሳን በኋላም አቡነ ሐራ በተወለዱ በ22ዐ ዓመታቸው በ11ዐዐ ዓ/ም ዐረፉ፡፡ የእርሳቸውንም ፈለግ አባ ፍሬ ሠናይ የተባሉ አባት ተከተሏቸው፡፡ ይህም ሥፍራ ዛሬ አርባራ መድኃኔዓለም ገዳም በመባል ይታወቃል፡:
በአሁኑ ወቅት ይህ ቦታ በተለያየ አፅፍ የተከፈኑ እና የተገነዙበትም
ማሠሪያ ክር በእጃቸውና
በእግራቸው ጣት ላይ የሚታይ ብዙ አፅሞች ይገኙበታል፡፡ ምንም እንኳን ዋሻው በአፅም የተሞላ ቢሆንም ከአካባቢው የሚወጣው መዓዛ ግን ከሙታን መንደር የሚገኝ መጥፎ ሽታ ሳይሆን (አልባብ አልባባ) የሚል መልካም መዓዛ ነው፡፡
የአካባቢው አረጋውያን እንደሚናገሩት ከሆነ ከኢጣሊያ ፋሺስት ወረራ በፊት ዘወትር የማኀሌት÷የከበሮና የዕልልታ ድምፅ ይሰማበት ነበረ፡፡ በተጨማሪም እጅግ ግዙፍ የሆነ ነጭ አሞራ እየበረረ ወደ ዋሻው ሲገባ ማየት የዘወትር ክስተት ነበረ፡፡ ከዚያ ወዲህ ግን ይህ ነገር ብዙም አይታይም፡፡
ቦታውን ከአካባቢው ምእመናን ጋር የሚያገናኘው ሌላው ነገር ደግሞ መሬት ሰብል እንዳትሰጥ ሰብል አጥፊ ተባይ ሲነሣ፣ እንስሳቱ ወተት መስጠታቸውን ሲቀንሱ ገበሬዎቹ አፅሞቹ ካረፉበት ቦታ አፈሩን በመዝገን በማሳቸው ላይ ይበትናሉ፤ እንስሳቱንም ያሻሹበታል፡፡ እንደ እምነታቸውም እንደሚያደርግላቸው በየዓመቱ ጥር 13 ቀን የሚገባው የእንስሳትና የሰብል ውጤት ምሥክር ነው፡፡ ከዋሻው የሚወጣው መልካም መዓዛም አሁንም ያልተቀየረ መሆኑን ሄዶ የሚመለከት ምሥክር ነው፡፡
አባ ኖብ
ትውልዳቸው በሶሪያ ሲሆን ወደ ኢትዮጵያ ወጥተው ከአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ ጋር ተገናኙ፡፡ የኢትዮጵያውያንን ቋንቋና ባሕል ካጠኑ በኋላ በትግራይ ተንቤን ፀፀራ ወረዳ ከሚገኘው ዋሻ ላይ ቤተ ክርስቲያን ተክለው ገዳም መሠረቱ፡፡ ከዚያም ቀጥለው በመላ ኢትዮጵያ በመዘዋወር ገዳማትን መሥርተው በ11ዐዐ ዓ.ም. ኀዳር 8 ቀን ዐረፉ፡፡
አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ |
በኢትዮጵያ የምንኵስናና የገዳማት ታሪክ ውስጥ ከ3ኛው - 12ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ያለው ጊዜ በአብዛኛው ከውጭ በመጡ አበው ሥርዓተ ምንኵስና የተስፋፋበት ሲሆን ከ12ኛው-15ኛው ያለው ደግሞ ከመላ ኢትዮጵያ በተነሡ አበው ቅዱሳን ሥርዓተ ምንኵስናና የገዳማት ትክል ከሰሜን ወደ ምዕራብ፣ ምሥራቅና ደቡብ የተስፋፋበት ወቅት ነው፡፡
ዋቢ
1. ትንሣኤ ቁ.99/1978
2. ገድለ አባ ሊባኖስ
3. ገድለ አባ ዮሐንስ
4. ዜና መንዝ
5. የአንኰበር መሳፍንት የታሪክ መጽሐፍ
6. ትንሣኤ ቁ.11/79
7. ትንሣኤ ቁ.22/80
8. Conti Rossini, steria PL.XLIV
9. ሉሌ መላኩ፣ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ አ.አ 1986
10.
አባ ጎርጎርዮስ፤ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ
11.
አባ ጎርጎርዮስ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን
ታሪክ
ሐመር መጽሔት
ምንጭ:
http://www.melakuezezew.info/
No comments:
Post a Comment