በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ! አሜን!
“… ሕያውን ከሙታን መካከል ስለምን ትፈልጋላችሁ? ተነሥቶአል እንጂ በዚህ የለም ።” ሉቃስ ፳፬ ÷ ፭
ያለውናየነበረው የሚመጣውም ከሙታንም በኵርሆኖ የተነሣው በምድርና በሰማያትያሉትን ሁሉ የሚገዛ የነፍሳችንቤዛና እረኛ በርኅራኄው ብዛትየወደደን፣ ከኃጢአታችንም በከበረ ደሙያጠበን ቅዱሱ የማርያም ልጅከባሕርይ አባቱ ከአብ፣ ከባሕርይሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋርለዘለዓለም የተመሰገነ ይሁን! አሜን!
ተሳስተንበሠራነው ኃጢአት፣ በበደላችንም ምክንያትእንደ ደረቀ ቅጠል ከመርገምናከሞት ስር ወድቀን፣ ጽድቃችንእንደመርገም ጨርቅ ሆኖ ሳለቃልኪዳኑን የማይረሳ አምላክ ከሰማያትተመለከተ። ከአቤል ጀምሮ የፈሰሰውየቅዱሳን ደም፣ ከአዳም ጀምሮየቀረበው የኃጢአት መስዋዕት የአዳምንልጅ ሊያድነው እንዳልቻለ አየ።አዳምና ልጆቹ ለብዙ ዘመናትበመንፀፈ ደይን ወድቀው፤በዲያቢሎስ የባርነት ቀንበር ተይዘውበሲኦልና በግዞት መሰቃየታቸውንና ወደቀደመውርስት ለመመለስ መናፈቃቸውን አስተዋለ።ስለዚህም ከቅዱስነቱና ከክብሩ ማደሪያከጽዮን ጎበኘን።
እነሆ!የዘመኑ ፍፃሜ በደረሰ ጊዜ፣ለፍጥረቱ የሚገደው ጌታ እግዚአብሔርየመከራና የጭንቀት ቀናትን፣ የጉስቁልናናየሥቃይ፣ የጨለማና የጭጋግ ደመና ዘመናትን ያሳልፍ ዘንድ፤የተዋረደውን ሊያከብር፣ የወደቀውን ሊያነሣ፣የሞተውንም ሕይወት ይሰጥ ዘንድ፤በቸርነቱና በፍቅሩ በትህትናውም ብዛትሥጋን ለበሰ። መለኮት የሥጋንባሕርይ ገንዘብ አደረገ፣ የፈጠረውንምሥጋ ተዋሐደ። ከኃጢአትም በቀርፍፁም ሰው ሆነ። የንጋትኮከብ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስሁለተኛ ሰማይ ከሆነችው ከድንግልማርያም ተወለደ፤ የጽድቅ ፀሐይአምላክ፣ ከእውነተኛዋ ምሥራቅ ከብርሃንእናት ከድንግል ወጣ፤ በመላውዓለምም አበራ። የማይታየው ታየ፣ዘመን ዕድሜ የማይቆጠርለት ዘመንተቆጠረለት።
በ ፴ ዘመኑም በዕደ ዮሐንስ ተጠመቀ፤ በገዳመ ቆሮንቶስ ፵ መዓልትና ፵ ሌሊት ጾመ፤ ፈታኙንም ድል አደረገ። “ዘመኑ ተፈጸመ፤ የእግዚአብሔርም መንግሥት ቀርባለች፤ ንስሐ ግቡ፤ በወንጌልም እመኑ።” እያለ ወደገሊላ መጣ። ማርቆስ ፩÷፲፭ወንጌልን በእስራኤል አውራጃዎች ሰበከ፤በፊታቸውም ብዙ ድንቅና ተአምራትንአደረገ፤ ሕሙማንን ፈወሰ፣ ለምጻሞችንአነጻ፣ የዕውራንን ዓይን አበራ፣አንካሶች እንዲሄዱ ደንቆሮዎች እንዲሰሙ አደረገ፣ሙታንን አስነሣ። ለሰማያዊ መንግስትናለዘላለማዊ ሕይወት የሚያበቃውን የቤዛነትንቃል አስተማረ። ጥቂቶች በቃሉተመሩ፤ ብዙዎች ግን ሊያድናቸውናሊታደጋቸው ወደ አባቱም መንግሥትሊያፈልሳቸው እንደመጣ አላወቁም። ይልቁንምየአይሁድ አለቆችና ካህናት አብዝተውይቃወሙት ሊገድሉትም ያሴሩ ነበር።በምሴተ ሐሙስ እራት ከበሉበኋላ ቁጥሩና ዕድል ፈንታውከሐዋርያት ጋር የነበረው ይሁዳጌታን በመሳም ለአይሁድ አለቆችአሳልፎ ሰጠ። መስፍኑ ጲላጦስጌታ ከተከሰሰበት ጉዳይ አንዳችእውነት ባላገኘ ጊዜ ሊፈታውወደደ። የካህናት አለቆች ግንሕዝቡን አሳምፀው እንዲሰቀል ግድአሉት። ጌታም በሐሰት ፍርድለሞት ተላልፎ ተሰጠ። በመስቀልምቸነከሩት፣ እርሱ ግን የፍቅርአምላክ ነውና በመስቀል ላይሆኖም “የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው” በማለትቸርነቱን ገለጠላቸው። በእርሱ ቁስልእንድንፈወስ፣ በሕማሙ ድኅነት እንዲሆንልን፤ በሞቱ ሕይወትን እንድናገኝ፣በፈቃዱ ታመመ፣ መከራን ተቀበለእንጂ የሰው ልጅ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ምንም ነገርማድረግ አይቻለውም ነበር። ጌታችንናመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሙታንንያድን ዘንድ ሞተ፣ የሞትንናየዲያብሎስን ኃይል በሥልጣኑ ሽሮበሰንበት ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፤ክብርና ምሥጋና ለእርሱ ይሁን!አሜን!