Sunday, April 1, 2012

"የበገና አገልግሎት በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን"


"የበገና አገልግሎት በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን"

በገና የኢትዮጵያ /ክርስቲያን የምስጋና መሳሪያ

በገና 
"በገና"- እንደሌሎች የሃገራችን ጥልቅ ብሔራዊ የታሪክ ሃብቶችና በታሪክም ከእስራኤል ቀጥሎየኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ብቸኛ ጥንታዊ የዜማ መሣርያ ጥንታዊ ይዘቱን የጠበቀ የሀገር ሀብት እንደመሆኑ መጠን ሁለት ዓይነት ትርጉም አለው፡፡
እነርሱም፡-
1. ሰዋስዋዊ ትርጉምና
2. ሥነ ቃላዊ ትርጉም.............. ይባላሉ፡፡
1. የበገና ሰዋስዋዊ ትርጉም
"በገና" የሚለው ስምና "በገነ" የሚለው ግሥ በተለያዩ መዝገበ ቃላትና የቋንቋ ሊቃውንት ተተርጉሞእናገኛለን፡፡ ለምሳሌ፡- አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ"መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ መዝገበ ቃላት ሐዲስ"በሚል መጽሐፋቸው በሁለት መልኩ ማለት "ሲጠቅብና ሲላላ" ብለው በማመሳጠር እንዲህብለውተርጉመውታል፡፡
በገና - በዕብራይስጥ ናጌን ይባላል ካሉ በኋላ ሲተረጉሙት - ነዘረ፣ መታ፣ ደረደረ፣ ማለትነው፡፡ ሲጠብቅ ግን - ነደደ፣ ተቆጣ... ያሰኛል ብሏል፡፡
በገና፡ - በቁሙ መዝሙር ማለት ነው ብለውም ፈትተውታል፡፡ (አለቃ ኪዳነ ወልደ ክፍሌ፡መጽሐፈ ስዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ)


አባ ዮሐንስ /እግዚአብሔር የትግርኛ መዝገበ ቃላት በተባለ መጽሐፋቸው፡- በገናን በቁሙ በገናብለው ተርጉመውታል፡፡ (አባ ዮሐንስ /እግዚአብሔር፣ ትግርኛ አማርኛ መዝገበ ቃላት፣1948፣አሥመራ)
ከሳቴ ብርሃን ተሰማ "የአማርኛ መዝገበ ቃላት" በተሰኘ መጽሐፋቸው እንዲህ ዓይነት ትርጉምሰጥተውታል፡፡
በገና፡- በአሥር አዉታር ጅማት በገናን ሠራ፣ ቃኘ፣ ደረደረ፣ ድምጽን እያጣራ፣ እያጣቀሰ፣እየነዘረ... በገናን በገነ... ካሉ በኋላ በገነኛ፡- የሚለው ደግሞ በገናንየሚመታ፣ በገናን የሚያውቅደርዳሪ... ማለት ነው ብለው ተርጉመውታል፡፡ (ከሳቴ ብርሃን ተሰማ፣ የአማርኛ መዝገበቃላት፣ 1951 .ም፣ አርቲስቲክማተሚያ ቤት፣ አዲስ አበባ)

2. የበገና ሥነ ቃላዊ ትርጉም፡-

በገነ፡- አደረቀ፣ አቃጠለ፣ አነደደ... ማለት ነው፡፡ በገናም ከዚህ የሚወጣ ስም ነው፡፡የዚህትርጉም ማግኘት ዋና ምክንያትም ሁሉም ነገር (የበገና ሁለገብ ሰውነት) በደረቅ ነገሮችማለትምበደረቅ እንጨትና በደረቅ ቆዳ እንዲሁም በደረቅ ጅማት የሚሠራ ወይም የሚዘጋጅ ስለሆነበገና ተባለ ተብሎ ይተረጐማል፡፡
በገና፡- "" እና "ገና" በመነጣጠል የሚያስገኘው ትርጉም በመጠቀም... ... ገና.... በገና በዓል ወይበገና ወቅት የሚደረደር የምስጋና መሣርያ ስለሆነ በገና ተባለ ተብሎ ይተረጎማል፡፡
በገና፡- በገነ ማለት ደረደረ ማለት ነው፡፡ ስለሆነም በገና ማለት ድርደራ፣ ምስጋና፣ መዝሙር...ማለት ነው መጽሐፍ ቅዱሳዊ መረጃ መሠረት በማድረግ ይተረጎማል፡፡ ለምሳሌ፡-
"አቤቱ አምላኬ በበገና አመሰግናለሁ" መዝ.42/434
"ለእግዚኣብሔር በገና ደርድሩለት" መዝ.485
"እግዚኣብሔርን በመሰንቆ አመስግኑት አሥር አውታር ባለው በበገናዘምሩለት" መዝ.32/332
የዚህ አጭር ጥናታዊ ጽሑፍ ኣቅራቢ ግን ከሁለቱም ወገን በሚወሰዱ የትርጉም መመሳሰል በመነሳትበምስጢር ከበገና መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎትጋር የተሻለ ቀረቤታ ያለውን ትርጉም ቢሆንይመርጣል፡፡
በመሆኑም፡- በገነ፡- ደረደረ፣ መታ፣ አነዘረ.... ወዘተ ማለት ነው በሚለው መልካም ትርጉምይስማማል፡፡ ምክንያቱም ከነባራዊ የበገና ማኅበራዊም ሆነ መንፈሳዊ እሴት ማለትም ከድርጊቱ ወይምከአቀራረቡ (ከአገልግሎቱ) ጋር አብሮ ይሄዳልና ነው፡፡ ከዚህ በመነሳት፡-

በገና፡ -ማለት ድርደራ፣ ምስጋና፣ መዝሙር... ወዘተ ማለት ነው፡፡ በገነኛው ቅዱስ ዳዊትበመዝሙሩ በገናን ሲተረጉም መዝሙር፣ ምስጋና... በማለት ሲገልጽ እናገኘዋለንና፡፡

የበገና ታሪካዊ አጀማመር፡-

በገና፡- በትክክል መቼና እንዴትተጀመረ የሚለው ጥያቄ መልሱ ከባድ ቢሆንም ሁላችንምእንደምናውቀው፣ ዓለምም ቢሆን በስፋት በግልጽ በአደባባይ እያወደሰው እንዳለ የሁሉም ጥበባትማለትም ሥጋዊ ጥበብንም ጨምሮ መገኛቸው ወይም ምንጫቸው መጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡ በመሆኑምበመጽሐፍ ቅዱስ ለመጀመሪያ ጊዜ ተገል የምናገኘው የምስጋና ወይም የዜማ መሣሪያ በገና ብቻነው፡፡

እንደ መጽሐፍ ቅዱስ እውነታ የመረመርነው እንደ ሆነ፡-

በገና ለመጀመሪያ ጊዜ የደረደሩት የላሜህ ልጅ የዩባል /ኢዮቤል/ ልጆች ነበሩ (ዘፍ.419-24)፡፡ይኸውም ዓይነ ስውር (ማየት የተሳነው) የነበረ ላሜህ አያታቸው በበረሃ እየሄደ እያለ ቃኤልተቅበዝባዥ ነበርና ለብቻው በዱር ተሰውሮ ሲንኮሻኮሽ ሰምቶ መንገድ ይመራው ለነበረው ረድእ "እጄይሞቅብኛል ቅጠሎች ሲንኮሻኮሹ እሰማለሁ አራዊት መጥቶብናል መሰለኝ ስለዚህ ድንጋይ አቀብለኝ"ኣለውና ድንጋዩን ተቀብሎ ቢወረውር የቃየን ግንባሩን መትቶ ገደለው፡፡ ቀርበው ሲመለከቱት የራሱአባት ቃየን ሆኖ ሲያገኘው እጅግ መሪርየሆነ ለቅሶ አለቀሰ፡፡ ወደ ቤቱ ተመልሶም ዓዳና ሴላ ለሚባሉትሚስቶቹ "ስምዓኒ ዓዳ ወሴላ አንስትያየ አነ ቀተልክዎ ለቃየን አቡየ፡- ዓዳና ሴላ ሚስቶቼ ሆይ ስሙኝ፤እኔ ዛሬ አባቴ ቃየንን ገድየዋለሁና...." በማለት ነገራቸው፡፡ እነርሱም የሆነውን ሁሉ ታሪካዊ ተዋረዱንጠብቀው የታሪክ እውነታውን ለልጆቻቸው ተናግረዋል፡፡ በዚህም የላሜህ የልጅ ልጆች (የዩባልልጆች) በቃየን ሞት ብቻሳይሆን በወላጆቻቸው የአሟሟት ሁኔታ እጅግ አዘኑ፡፡ ይህም አቤል በቅንዓትምክንያት በገዛ ወንድሙ በቃኤል መገደሉ፤ ቃየንም "ተባርዮን የማያስቀር አምላክ ነውና" በገደለውዓይነትየአገዳደል ዘይቤ በድንጋይ በልጁ በላሜህ መሞቱ... እያወጡ እያወረዱ እጅግ ከማዘናቸውየተነሳ በገና ለመጀመርያ ጊዜ ከደረቁ ቁሳቁሶች አበጅተው በመሥራት በበገና እያንጎራጎሩ ሐዘናቸውንገልጸዋል፡፡

በዚህም በገና ከፍጥረተ ዓለምብዙም ባልራቀ ሁኔታ (ከአዳም አምስተኛ ልጆች በሆኑ አበው) የተገኘየመጀመርያ የሐዘን፣ የእንጉርጉሮ፣ የንስሐ፣ የልመናና የምስጋና መሣሪያ ነው እንላለን፡፡ተዋረዱም፤
አዳም፡- ቃኤልን ይወልዳል ቃኤል፡- ላሜህን ይወልዳል ላሜህ፡- ዮባልን ይወልዳል ዮባል፡- በገናየሚደረድሩትን ይወልዳል (ስማቸው በመጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ አልተገለጸም)፡፡ በመሆኑም የአራተኛትውልድ ልጆች ማለትም ከአዳም አምስተኛ ትውልድ በሆኑት በእነዚህ አበው ምክንያት በገናንተዘጋጅቶ መደርደር ተጀመረ፡፡

ቃለ በገና፡- ቃለ ማኅዘኒ

ድምፀ ማኅዘኒ ... ነው፡፡ ምክንያቱም በተለይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሊቃውንትአራቅቀው እንደሚተረጉሙት ይህ ምድራዊ ማኅዘኒ ዜማ የመጣው በዮባል ልጆች ኃዘንና እንጉርጉሮምክንያት እንደሆነ ይኸው ከላይ የተጠቀሰው ታሪክ ጠቅሰው ያትታሉ፣ ያመሰጥራሉ፡፡ ይኸውም ከላይእንደተገለጸው፡- ቃየል ወንድሙ አቤልን መግደሉ፤ ቃየል ደግሞ በልጁ በላሜህ መገደሉን፤እያስታወሱ የዩባል ልጆች የደረቀ እንጨት ጠርበውና አለዝበው፣ ቆዳ ወጥረው፣ ፍቀው፣አድርቀውና ዳምጠው፣ ጅማት አክርረውና አበግነው... በቃለ ማኅዘኒ፣ በድምፀ ማኅዘኒ... ያንጐራጉሩነበር በማለት ሊቃውንቶቻችን ያትታሉ፡፡ በዚህ ታሪካዊ እውነታ ምክንያት ነው "በገና" ቃለ ማኅዘኒ፣ድምጸ ማኅዘኒ ሆኖ የሐዘን ማለትም የንስሐ፣ የልመናና የምስጋና ማቅረቢያ የዜማ መሣሪያ በመሆንአገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኘው፡፡ የበገና የአጀማመሩ ታሪክ በዩባል ልጆች ቢሆንም ዘመናትአልፎ ከትውልድ ትውልድ ሲተካ ይዘቱም ሆነ ዓይነቱ እየተሸሻለ መጥቶ የበገና አጠቃላይ ማኅበራዊሚናውም ሆነ መንፈሳዊ አገልግሎት ይበልጥ ጎልቶ የታወቀው ግን በመዝሙረኛው (በበገነኛው) በቅዱስዳዊት ምክንያት ነው፡፡

የበገና አገልግሎት፤

በገና የሚያገለግለው ለመንፈሳዊትሩፋት ማለትም ለምስጋናና ለልመና ብቻ ነው፡፡ በመሆኑም ተመርጦለቤተክርስቲያን አገልግሎት ይውላል፡፡ ለምሳሌ፡-
"አቤቱ አምላኬ በበገና አመሰግንሀለሁ" መዝ.42/43/4
"አሥር አውታርም ባለው በበገና ዘምሩለት" መዝ.32/33/2
"ለእግዚአብሔር በገና ደርድሩለት" መዝ.4.8/5/... ወዘተ ከተመዘገቡት መጽሐፍ ቅዱሳዊመረጃዎች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
ከዚህ በተጨማሪም እንደ አስፈላጊነቱ ለማኅበራዊ እሴት፣ ለሃገር ክብር፣ ለሉዓላዊነት... በገናይደረደራል፡፡ ለዚህ ጥሩ ማስረጃችን በአፄ ቴዎድሮስ ጊዜ የተደረደረውና እስከ አሁን ድረስ የበገናመማርያ የሆነው የበገና አገልግሎት ነው፡፡ ከዚህ ውጭ በገና ለዓለማዊ ፍላጐት ማስፈጸሚያማለትም፡- ለዳንስና ለዳንኪራ ለዘፈንና ለጭፈራ ለዝናና ለጉራ ለቀልድና ለፉከራ ... ወዘተ ፈጽሞአገልግሎት አይሰጥም፡፡

የበገና ጥቅም፡-

ከላይ እንደተገለጸው በገና በዋናነት ለመለኮታዊ የእግዚአብሔር ፈቃድ ማስፈጸሚያማለትም ለምስጋናናለልመና የሚያገለግል ሲሆን በተጨማሪም ለማኅበራዊ እሴት መግለጫ የሚውል መንፈሳዊና ጥንታዊየዜማ መሣሪያ ነው፡፡ ለምሳሌ፡- እግዚአብሔርን ለማመስገን እና እግዚአብሔርን ለመለመን። ስለበገና በመጽሐፍ ቅዱስ የተጻፉ በአብዛኞቹ የሚገልጹት "በገና ለምስጋናና ለልመና ሲቀርብ" ነው

ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ማውጫ ያገኘኋቸው እነሆ፡ የሚከተሉትን መመልከት ይቻላል ኦሪት ዘፍጥረት
421 “የወንድሙም ስም ዩባል ነበረ እርሱም በገናንና መለከትን ለሚይዙ አባት ነበረ።
3127 “ስለምን በስውር ሸሸህ? ከእኔም ከድተህ ስለምን ኮበለልህ? በደስታና በዘፈን በከበሮና በበገናእንድሰድድህ ለምን አልነገርኸኝም?”

መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ

105 “ከዚያም በኋላ የፍልስጥኤማውያን ጭፍራ ወዳለበት ወደ እግዚአብሔር ኮረብታ ትመጣለህወደዚያም ወደከተማይቱ በደረስህ ጊዜ፥ በገናና ከበሮ እምቢልታና መሰንቆ ይዘው ትንቢት እየተናገሩከኮረብታው መስገጃ የሚወርዱ የነቢያት ጉባኤ ያገኙሃል።
1616 “በገና መልካም አድርጎ የሚመታ ሰው ይሹ ዘንድ ጌታችን በፊቱ የሚቆሙትን ባሪያዎቹንይዘዝ ከእግዚአብሔርም ዘንድ ክፉ መንፈስ በሆነብህ ጊዜ በእጁ ሲመታ አንተ ደኅና ትሆናለህ አሉት።
1617 “ሳኦልም ባሪያዎቹን፦ መልካም አድርጎ በገና መምታት የሚችል ሰው ፈልጋችሁ አምጡልኝአላቸው።
1618 “ከብላቴኖቹም አንዱ መልሶ፦ እነሆ፥ መልካም አድርጎ በገና የሚመታ የቤተ ልሔማዊውንየእሴይን ልጅ አይቻለሁ እርሱምጽኑዕ ኃያል ነው፥ በነገርም ብልህ፥ መልኩም ያማረ ነው፥እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነውአለ።
1623 “እንዲህም ሆነ ከእግዚአብሔር ዘንድ ክፉ መንፈስ በሳኦል ላይ በሆነ ጊዜ ዳዊት በገና ይዞበእጁ ይመታ ነበር ሳኦልንም ደስ ያሰኘው ያሳርፈውም ነበር፥ክፉ መንፈስም ከእርሱ ይርቅ ነበር።
1810 “በነጋውም ሳኦልን ክፉ መንፈስ ከእግዚአብሔር ዘንድ ያዘው፥ በቤቱም ውስጥ ትንቢትተናገረ።ዳዊትም በየቀኑ ያደርግ እንደ ነበረ በእጁ በገና ይመታ ነበር። ሳኦልም ጦሩን በእጁ ይዞ ነበር።
199 “ሳኦልም ጦሩን ይዞ በቤቱ ተቀምጦሳለ ክፉ መንፈስ ከእግዚአብሔርዘንድ ያዘው። ዳዊትምበእጁ በገና ይመታ ነበር።
መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ
65 “ዳዊትና የእስራኤልም ቤት ሁሉ በቅኔና በበገና በመሰንቆም በከበሮም በነጋሪትና በጸናጽልበእግዚአብሔር ፊት በሙሉ ኃይላቸው ይጫወቱ ነበር።

መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ
1012 “ንጉሡም ከሰንደሉ እንጨት ለእግዚአብሔር ቤትና ለንጉሡ ቤት መከታ፥ ለመዘምራኑምመሰንቆና በገና አደረገ እስከ ዛሬም ድረስ እንደዚያ ያለ የሰንደል እንጨት ከቶአልመጣምአልታየምም።
መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ
315 “አሁንም ባለ በገና አምጡልኝ አለ። ባለ በገናውም በደረደረ ጊዜ የእግዚአብሔር እጅመጣችበት
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ
138 “ዳዊትና እስራኤል ሁሉ በቅኔና በበገና በመሰንቆና በከበሮ በጸናጽልና በመለከትበእግዚአብሔር ፊት በሙሉ ኃይላቸው ይጫወቱ ነበር።
1516 “ዳዊትም በዜማ ዕቃ በመሰንቆና በበገና በጸናጽልም እንዲያዜሙ፥ ድምፃቸውንም በደስታከፍ እንዲያደርጉ መዘምራኑን ወንድሞቻቸውን ይሾሙ ዘንድ ለሌዋውያን ኣለቆችተናገረ።
1521 “መቲትያ፥ ኤልፍሌሁ፥ ሚቅኒያ፥ ዖቤድኤዶም፥ ይዒኤል፥ ዓዛዝያ ስምንት አውታርባለው በገና ይዘምሩ ነበር።
1528 “እንዲሁ እስራኤል ሁሉ እያሉ ቀንደ መለከትና እምቢልታ እየነፉ፥ ጸናጽልና መሰንቆምበገናም እየመቱ፥ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት አመጡ።
165 “አለቃው አሳፍ ነበረ ከእርሱም በኋላ ዘካርያስ፥ ይዒኤል፥ ሰሚራሞት፥ ይሒኤል፥መቲትያ፥ ኤልያብ፥ በናያስ፥ ዖቤድኤዶም፥ ይዒኤል በመሰንቆና በበገና አሳፍም በጸናጽል ይዘምሩነበር።
251 “ዳዊትና የሠራዊቱ አለቆችም ከአሳፍና ከኤማን ከኤዶታም ልጆች በመሰንቆና በበገናበጸናጽልም ትንቢት የሚናገሩትን ሰዎች ለማገልገል ለዩ በአገልግሎታቸውም ሥራ የሠሩ ሰዎች ቍጥርይህ ነበረ።
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ
512 “መዘምራንም የነበሩት ሌዋውያን ሁሉ፥ አሳፍና ኤማን ኤዶታምም ልጆቻቸውምወንድሞቻቸውም፥ ጥሩ በፍታ ለብሰው ጸናጽልና በገና መሰንቆም እየመቱ በመሠዊያው አጠገብበመሥራቅ በኩል ቆመው ነበር ከእነርሱም ጋር መቶ ሀያ ካህናት መለከት ይነፉ ነበር። ካህናቱምከመቅደሱ በወጡ ጊዜ፥
911 “ንጉሡም ከሰንደሉ እንጨት ለእግዚአብሔር ቤትና ለንጉሡ ቤት ደርብ፥ ለመዘምራኑምመሰንቆና በገና አደረገ እንደዚህም ያለ በይሁዳ ምድር ከቶ አልታየም ነበር።
2028 “በበገናም በመሰንቆም በመለከትም ወደ ኢየሩሳሌም ወደእግዚአብሔርም ቤት ገቡ።
2925 “ይህንም ትእዛዝ እግዚአብሔር በነቢያቱ እጅ አዝዞአልና እንደዳዊትና እንደ ንጉሡ ባለራእይ እንደ ጋድ፥ እንደ ነቢዩም እንደ ናታን ትእዛዝ፥ ጸናጽልናበገና መሰንቆም አስይዞ ሌዋውያንንበእግዚአብሔር ቤት አቆመ።

መጽሐፈ ነህምያ
1227 “የኢየሩሳሌምንም ቅጥር በቀደሱ ጊዜ ቅዳሴውን በደስታና በምስጋና በመዝሙርምበጸናጽልም በበገናም በመሰንቆም ለማድረግ ወደ ኢየሩሳሌም ያመጡአቸው ዘንድ ሌዋውያኑንበየስፍራቸው ሁሉ ፈለጉ።
መዝሙረ ዳዊት
332 “እግዚአብሔርን በመሰንቆ አመስግኑት፥ አሥር አውታርም ባለው በበገና ዘምሩለት።
434 “ወደ እግዚአብሔር መሠዊያ፥ ጕልማስነቴንም ደስ ወዳሰኛት ወደ አምላኬ እገባለሁ አቤቱአምላኬ፥ በበገና አመሰግንሃለሁ።
494 “ጆሮዬን ወደ ምሳሌ አዘነብላለሁ፥ በበገናም ምሥጢሬን እገልጣለሁ።
540 “ለመዘምራን አለቃ በበገናዎች ዜፋውያን መጥተው ለሳኦል፦ እነሆ ዳዊት በእኛ ዘንድ ተሸሽጓል ብለው በነገሩት ጊዜ

የዳዊት ትምህርት።
550 “ለመዘምራን አለቃ በበገናዎች የዳዊት ትምህርት።
578 “ክብሬ ይነሣ፥ በገናና መሰንቆም ይነሡ እኔም ማልጄ እነሣለሁ።
61 “ለመዘምራን አለቃ በዎች የዳዊት መዝሙር።
67 “ለመዘምራን አለቃ በበገናዎች የዳዊት መዝሙር።
7122 “እኔም በበገና ስለ እውነትህ አመሰግንሃለሁ የእስራኤል ቅዱስ አምላክ ሆይ፥ በመሰንቆ እዘምርልሃለሁ።
76 “ለመዘምራን አለቃ በበገናዎች ስለ አሦራውያን የአሳፍ የምስጋና መዝሙር።
812 “ዝማሬውን አንሡ ከበሮንም ስጡ፥ ደስ የሚያሰኘውን በገና ከመሰንቆ ጋር
923 “አሥር አውታር ባለው በበገና፥ ከምስጋና ጋርም በመሰንቆ።
1082 “በገና ሆይ፥ ተነሥ፥ መሰንቆም እኔም ማልጄ እነሣለሁ።
1449 “አቤቱ፥ አዲስ ቅኔ እቀኛልሃለሁ አሥር አውታር ባለው በገና እዘምርልሃለሁ።
1503 “በመለከት ድምፅ አመስግኑት በበገናና በመሰንቆ አመስግኑት።

ትንቢተ ኢሳይያስ
512 “መሰንቆና በገና ከበሮና እምቢልታም የወይን ጠጅም በግብዣቸው አለ የእግዚአብሔርን ሥራ ግን አልተመለከቱም፥ እጁም ያደረገችውን አላስተዋሉም።
1410 “እነዚህ ሁሉ። አንተ ደግሞ እንደእኛ ደክመሃልን? እኛንስ መስለሃልን? ጌጥህና የበገናህ ድምፅ ወደ ሲኦል ወረደ

ሰቆቃው ኤርምያስ
514 “ሽማግሌዎች ከአደባባይ፥ ጕልማሶች ከበገናቸው ተሻሩ።

ትንቢተ ሕዝቅኤል
3332 “እነሆ፥ አንተ መልካም ድምፅ እንዳለው እንደሚወደድ መዝሙር ማለፊያም አድርጎ በገና እንደሚጫወት ሰው ሆነህላቸዋል ቃልህንም ይሰማሉ ነገር ግን አያደርጉትም።

ትንቢተ ዳንኤል
35 “የመለከትንና የእንቢልታን፥ የመሰንቆንና የክራርን፥ የበገናንና የዋሽንትን፥ የዘፈንንም ሁሉ ድምፅ በሰማችሁጊዜ፥ ተደፍታችሁ ንጉሡ ናቡከደነፆር ላቆመው ለወርቁ ምስል እንድትሰግዱ ታዝዛችኋል።
37 “ስለዚህ በዚያን ጊዜ አሕዛብ ሁሉየመለከቱንና የእንቢልታውን፥ የመሰንቆውንና የክራሩን፥ የበገናውንና የዘፈኑንም ሁሉ ድምፅ በሰሙ ጊዜ፥ ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የተናገሩ ሁሉ ተደፉ፥ ንጉሡም ናቡከደነፆር ላቆመው ለወርቅ ምስል ሰገዱ።
310 “አንተ፥ ንጉሥ ሆይ። የመለከትንና የእንቢልታን፥ የመሰንቆንና የክራርን፥ የበገናንና የዋሽንትን፥ የዘፈንንም ሁሉ ድምፅ የሚሰማ ሰው ሁሉ ተደፍቶ ለወርቁ ምስል ይስገድ
315 “አሁንም የመለከቱንና የእንቢልታውን የመሰንቆውንና የክራሩን የበገናውንና የዋሽንቱን የዘፈኑንም ሁሉ ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ ተደፍታችሁላሠራሁት ምስል ብትሰግዱ መልካም ነው ባትሰግዱ ግን በዚያ ጊዜ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ትጣላላችሁ ከእጄስየሚያድናችሁ አምላክ ማን ነው? ብሎ ተናገራቸው።

የዮሐንስ ራእይ
58 “መጽሐፉንም በወሰደ ጊዜ አራቱ እንስሶችና ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት ወደቁ፥ እያንዳንዳቸውም በገናንና የቅዱሳን ጸሎት የሆነ ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ዕቃ ያዙ።
142 “እንደ ብዙ ውኃም ድምፅና እንደ ታላቅ ነጐድጓድ ድምፅ ያለ ከሰማይ ድምፅን ሰማሁ፥ ደርዳሪዎችም በገና እንደሚደረድሩ ያለ ድምፅ ሰማሁ።
152 “በእሳትም የተቀላቀለውን የብርጭቆ ባሕር የሚመስለውን አየሁ፥ በአውሬውና በምስሉም በስሙም ቍጥር ላይ ድል ነሥተው የነበሩት የእግዚአብሔርን በገና ይዘው በብርጭቆ ባሕር ላይ ሲቆሙ አየሁ።
1822 “በገና የሚመቱና የሚዘምሩም ድምፅ እንቢልታንና መለከትንም የሚነፉ ድምፅ ከእንግዲህ ወዲህበአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፥ የእጅ ጥበብም ሁሉ አንድ ብልሃተኛ እንኳ ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይገኝም፥ የወፍጮ ድምጽም ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥከቶ አይሰማም፥

ትንቢት ለመናገር
ቅዱስ ዳዊት የተናገራቸው ቃለ ትንቢቶች በሙሉ መመልከት ወይም ማንበብ በቂ ነው፡፡
"ወደዚያም ወደ ከተማይቱ በደረስህ ጊዜ፥ በገናና ከበሮ እምቢልታና መሰንቆ ይዘው ትንቢት እየተናገሩ ከኮረብታው መስገጃ የሚወርዱ የነቢያት ጉባኤ ያገኙሃል" 1 . መሳ. 105
ከመናፍስት ሥቃይ ለመዳን
"እንዲህም ሆነ ከእግዚአብሔር ዘንድ ክፉ መንፈስ በሳኦል ላይ በሆነ ጊዜ ዳዊት በገና ይዞ በእጁ ይመታ ነበር፡፡ ክፉ መንፈስም ከእርሱ ይርቅ ነበር" (1ኛሳሙ.1623) እንዲል፡፡
የሀገር ሉዓላዊነት ለመግለጽ ... ወዘተ ይጠቅማል፡፡
"ፈረሱ አባ ታጠቅ ስሙ ቴዎድሮስ..... እኔ መዩ ቱርክን ባይ የምሸሽ ነኝ ወይ...." እንደ ምሳሌ ልንወስደው እንችላለን፡፡

በገና ወደ ሀገራችን እንዴት መጣ?
የበገና ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ የአመጣጥ ታሪክ ሁለት ዓይነት አመለካከቶች አሉ፡፡
1. የሀገራችን ኢትዮጵያ የሥልጣኔዋ ውጤትና በሕገ ልቡና የማመንዋ ውጤት ነው፡፡ /የተጀመረ እዚሁ ሀገራችን ነው የሚል አስተምህሮ ነው፡፡/
2. በቀዳማዊ ምኒሊክ ጊዜ ከታቦተጽዮን ጋራ አብረው ከመጡት የዜማና የሥርዓተ አምልኮ ንዋያተ ቅድሳት፣ መጻሕፍት... ወዘተ አንድ ሆኖ የመጣ ነው የሚሉ ሲሆን ይህንኑ አመለካከትም ይበልጥ በሀገራችንጠበብት ሊቃውንት በስፋት ይተረጉማል፣ ይተረካል... ይታመናልም፡፡

የበገና አሠራር፡-
በገና የሚሠራው፡-
ከደረቀ እንጨት /ተጠርቦና ለዝቦ እንዲሁም በልዩ ጥበብ ተውቦ/
ከደረቀ ቆዳ፡- /ተፍቆና ተዳምጦ እንዲሁም ዙሪያውን ተሰፍቶ/
ከደረቀ ጅማት፡- /በግኖና ከርሮ ከላይ እስከ ታች ተወጥሮ፣በቁጥር ተቀምሮ ይሠራል፡፡/

የበገና አቀራረብ ዘዴዎች፡-
በገና በሁለት መልኩ ሊቀርብ ወይሊደረደር ይችላል፡፡
1. በእጅና፡-
2. በድሕንጻ፡- (ድሕንጻ፡- መግረፊያ ሆኖ እጅግ መሳጭና የበለጠ በሚመስጥ መልኩ በገናውን የሚያስጮኽ ጥንታዊ የዜማ መሣርያ ወይም የበገና ማጫወቻ ነው) "በድሕንጻ መንፈስ ዝብጢ አውታረመሰንቆሁ ለልብየ ወአስተንፍሲ ውስተ አፉየ ከመ እኩን እንዚራሁለበኩርኪ......) እንዲል (መጽሐፈ ሰዓታት፡ እሴብሕ ጸጋኪ ይመልከቱ)

ከበገና ምሳሌያዊ ትምህርቶች፡-
ላይኛው፡- የፈቃደ እግዚአብሔር
ታችኛው፡- የማኅፀነ ድንግል
ግራና ቀኙ፡- የሚካኤልና የገብርኤል
አሥሩ አውታር፡- የዓሠርቱ ቃላት
አውታሩ በእጅ ሲመታ ሁለቱም ማለትም አውታሩንና እጁን ተዋሕደው ድምፁ የሚሰማው ከታችኛው (ከቆዳው) ዘንድ እንደ ሆነ ሁሉ መለኮትና ሥጋ ተዋሕደውከማኅፀነ ድንግል ዘንድ ለማደራቸው ምሳሌ ነው፡፡
አንድም፡-
ላይኛውና ታችኛው፡- የሰማይና የምድር
ግራና ቀኙ፡- የብሉይና የሐዲስ
አሥሩ አውታር፡- የዓሠርቱ ትእዛዛት
በብሉይ ኪዳን ፈጣሪና ፍጡርንየሚያገናኙ ዓሠርቱ ትእዛዛት ስለነበሩ በዚሁ ተመስሏል፡፡

የበገና ቅኝቶ፡-
በገና ሦስት ዓይነት ቅኝት አለው፡፡ እነርሱም፡-
1. በበገና ቅኝት ሰላምታ በተለምዶ አምባሰል እንደሚባለውነው፤
2. በበገና ቅኝት እርግብና ዋኔንበተለምዶ ትዝታ እንደሚባለው ነው፤
3. በበገና ቅኝት ስለቸርነትህ በተለምዶ አንቺ ሆዬ ለኔ እንደሚባለው ነው፤
በተለምዶ ያልኩበት ምክንያት በሌሎች የዜማ መሣርያ (በዘፈን መሣርያዎች) የሚሰጣቸው ስም ሲሆን በገና ደግሞ የራሱ የሆነ መንፈሳዊ አገልግሎት የሚያበረክትበት የራሱ መዝሙርናየቅኝት ስልት ያለው እድሜ ጠገብቅርስ በመሆኑ "በተለምዶና በበገና" ተብለው ቀርበዋል፡፡ ከሁለቱም በአንዱ ግልጽ እንዲሆን ታስቦ ብቻ ነው፡፡ በመጨረሻ ስለ በገና ለወደፊት ሰፊ ነገር የምለው ነገር ቢኖረኝም ግን ለጊዜው ለማጠቃለል ያህል፡-

በበገና፡-
እግዚአብሔር፡- ይመሰገንበታል፣ ይቀደስበታል፣ ይለመንበታል... ፡፡
ቅዱሳን፡- ይከበሩበታል፣ ይታሰቡበታል... ፡፡
ሕሙማን፡- ይፍወሱበታል፡፡
ሕዙናን፡- ይጽናኑበታል፡፡
አማኞች፡- ይመከሩበታል፡፡
የሀገረ ክብር፡- ይገለጽበታል፣ ይነገርበታል... እያልኩ ለወደፊትበገና እንዴት እንደሚደረደር ለማሳየትና የድምጹን ሁኔታ ለማስተማር በድምጽ፣ እንዲሁም በድምጽ ወምስል ለማዘጋጀት ሐሳብ አለ፤ ሁሉን የሚፈጽም ግንእግዚአብሔር ስለሆነ የዚህ ታሪካዊና ጥንታዊ የዜማ መሣርያ ጣዕም ለሥርዓተ አምልኮ፣ ለልመናና ለምስጋና ተጠቅመንበትሕይወታችን በንስሐ መርተን ፍጻሜአችን ያማረ የተስተካከለ እንዲሆንልን አምላከ ዳዊት እግዚአብሔር ይርዳን፤ የወላዲተአምላክ ድንግል ማርያም ጣዕም በአንደበታችን ፍቅርዋንም በልቡናችን ይሣልልን፡፡ አሜን!
           


ምንጭ፡  http://gech-tewahedo.blogspot.com/2012/03/blog-post_6768.html
እባክዎን ለራስዎና ለጓደኞችዎ ያካፍሉት:  

No comments:

Post a Comment