በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ! አሜን!
“… ሕያውን ከሙታን መካከል ስለምን ትፈልጋላችሁ? ተነሥቶአል እንጂ በዚህ የለም ።” ሉቃስ ፳፬ ÷ ፭
ያለውናየነበረው የሚመጣውም ከሙታንም በኵርሆኖ የተነሣው በምድርና በሰማያትያሉትን ሁሉ የሚገዛ የነፍሳችንቤዛና እረኛ በርኅራኄው ብዛትየወደደን፣ ከኃጢአታችንም በከበረ ደሙያጠበን ቅዱሱ የማርያም ልጅከባሕርይ አባቱ ከአብ፣ ከባሕርይሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋርለዘለዓለም የተመሰገነ ይሁን! አሜን!
ተሳስተንበሠራነው ኃጢአት፣ በበደላችንም ምክንያትእንደ ደረቀ ቅጠል ከመርገምናከሞት ስር ወድቀን፣ ጽድቃችንእንደመርገም ጨርቅ ሆኖ ሳለቃልኪዳኑን የማይረሳ አምላክ ከሰማያትተመለከተ። ከአቤል ጀምሮ የፈሰሰውየቅዱሳን ደም፣ ከአዳም ጀምሮየቀረበው የኃጢአት መስዋዕት የአዳምንልጅ ሊያድነው እንዳልቻለ አየ።አዳምና ልጆቹ ለብዙ ዘመናትበመንፀፈ ደይን ወድቀው፤በዲያቢሎስ የባርነት ቀንበር ተይዘውበሲኦልና በግዞት መሰቃየታቸውንና ወደቀደመውርስት ለመመለስ መናፈቃቸውን አስተዋለ።ስለዚህም ከቅዱስነቱና ከክብሩ ማደሪያከጽዮን ጎበኘን።
እነሆ!የዘመኑ ፍፃሜ በደረሰ ጊዜ፣ለፍጥረቱ የሚገደው ጌታ እግዚአብሔርየመከራና የጭንቀት ቀናትን፣ የጉስቁልናናየሥቃይ፣ የጨለማና የጭጋግ ደመና ዘመናትን ያሳልፍ ዘንድ፤የተዋረደውን ሊያከብር፣ የወደቀውን ሊያነሣ፣የሞተውንም ሕይወት ይሰጥ ዘንድ፤በቸርነቱና በፍቅሩ በትህትናውም ብዛትሥጋን ለበሰ። መለኮት የሥጋንባሕርይ ገንዘብ አደረገ፣ የፈጠረውንምሥጋ ተዋሐደ። ከኃጢአትም በቀርፍፁም ሰው ሆነ። የንጋትኮከብ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስሁለተኛ ሰማይ ከሆነችው ከድንግልማርያም ተወለደ፤ የጽድቅ ፀሐይአምላክ፣ ከእውነተኛዋ ምሥራቅ ከብርሃንእናት ከድንግል ወጣ፤ በመላውዓለምም አበራ። የማይታየው ታየ፣ዘመን ዕድሜ የማይቆጠርለት ዘመንተቆጠረለት።
በ ፴ ዘመኑም በዕደ ዮሐንስ ተጠመቀ፤ በገዳመ ቆሮንቶስ ፵ መዓልትና ፵ ሌሊት ጾመ፤ ፈታኙንም ድል አደረገ። “ዘመኑ ተፈጸመ፤ የእግዚአብሔርም መንግሥት ቀርባለች፤ ንስሐ ግቡ፤ በወንጌልም እመኑ።” እያለ ወደገሊላ መጣ። ማርቆስ ፩÷፲፭ወንጌልን በእስራኤል አውራጃዎች ሰበከ፤በፊታቸውም ብዙ ድንቅና ተአምራትንአደረገ፤ ሕሙማንን ፈወሰ፣ ለምጻሞችንአነጻ፣ የዕውራንን ዓይን አበራ፣አንካሶች እንዲሄዱ ደንቆሮዎች እንዲሰሙ አደረገ፣ሙታንን አስነሣ። ለሰማያዊ መንግስትናለዘላለማዊ ሕይወት የሚያበቃውን የቤዛነትንቃል አስተማረ። ጥቂቶች በቃሉተመሩ፤ ብዙዎች ግን ሊያድናቸውናሊታደጋቸው ወደ አባቱም መንግሥትሊያፈልሳቸው እንደመጣ አላወቁም። ይልቁንምየአይሁድ አለቆችና ካህናት አብዝተውይቃወሙት ሊገድሉትም ያሴሩ ነበር።በምሴተ ሐሙስ እራት ከበሉበኋላ ቁጥሩና ዕድል ፈንታውከሐዋርያት ጋር የነበረው ይሁዳጌታን በመሳም ለአይሁድ አለቆችአሳልፎ ሰጠ። መስፍኑ ጲላጦስጌታ ከተከሰሰበት ጉዳይ አንዳችእውነት ባላገኘ ጊዜ ሊፈታውወደደ። የካህናት አለቆች ግንሕዝቡን አሳምፀው እንዲሰቀል ግድአሉት። ጌታም በሐሰት ፍርድለሞት ተላልፎ ተሰጠ። በመስቀልምቸነከሩት፣ እርሱ ግን የፍቅርአምላክ ነውና በመስቀል ላይሆኖም “የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው” በማለትቸርነቱን ገለጠላቸው። በእርሱ ቁስልእንድንፈወስ፣ በሕማሙ ድኅነት እንዲሆንልን፤ በሞቱ ሕይወትን እንድናገኝ፣በፈቃዱ ታመመ፣ መከራን ተቀበለእንጂ የሰው ልጅ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ምንም ነገርማድረግ አይቻለውም ነበር። ጌታችንናመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሙታንንያድን ዘንድ ሞተ፣ የሞትንናየዲያብሎስን ኃይል በሥልጣኑ ሽሮበሰንበት ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፤ክብርና ምሥጋና ለእርሱ ይሁን!አሜን!
ጌታችንበመዋዕለ ሥጋዌ መግቦቱ “ይህን ቤተመቅደስ አፍርሱት በሦስተኛውም ቀን አነሣዋለሁ”በማለት ስለትንሣኤው ተናግሮ ነበርሰሚዎቹ ባያስተውሉትም። ዮሐ፡ ፪፤፲፱ ዳግመኛም አይሁድ ምልክትንሲጠይቁት “… ከነቢዩም ከዮናስ ምልክትበቀር ምልክት አይሰጠውም፤ ዮናስበዓሣ አንበሪ ሆድ ሦስትቀንና ሦስት ሌሊት እንደነበረእንዲሁ የሰው ልጅበምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል” አላቸው።ማንም ግን አልተገነዘበውም። ማቴ፡፲፪÷፴፰-፵ ለሦስቱሕሩያን ሐዋርያት ፣ ለኤልያስናለሙሴ መለኮታዊ ክብሩን ከገለጠላቸውከደብረ ታቦር ሲወርዱ “የሰው ልጅ ከሙታን እስኪነሣ ድረስ ያያችሁትን ለማንም አትንገሩ።” ብሎአዘዛቸው። ማቴ፡ ፲፯÷፱
በባሕርዩሕማምና ሞት የሌለበት አምላክእኛን ሰለመውደዱ፤ የሥጋን ባሕርይገንዘብ በማድረጉ “ታመመ ፣ ሞተ”ተብሎ ተነገረለት። በትንሣኤውም የሞትንኃይልና ሥልጣን ሻረ። ሞቱናትንሣኤውም አማናዊ ነው። ጌታችንንሲያገለግሉ የነበሩት ሴቶች ከደቀመዛሙርቱ ጋር ሆነው፣ በሕማማቱናበሞቱ ሲያዝኑ ሰንብተው በተቀበረበሦስተኛው ቀን በማለዳ ተነስተውወደመቃብሩ ተጓዙ፤ ዛሬ በዕለተሰንበት የትንሣኤው ምሥራች ወደሚነገርባትና ወደሚከበርባት ቤተክርስቲያን በማለዳእንደምንሄደው! ታዲያ ሴቶቹ በዚህወቅት ነበር ያላሰቡትና ያልጠበቁትሁኔታ የተመለከቱት።የትልቁ ድንጋይ ከመቃብሩ በር መነሣት ፣ የጌታ ሥጋ መቃብሩ ውስጥ አለመኖር ፣ በመቃብሩ ውስጥ ጌታ ተገንዞበት የነበረውን የተልባ እግር ልብስ መገኘት ፣ ከሁሉም በላይ የትንሣኤውን ብሥራትከመላዕክት አንደበት መስማት። አራቱ ወንጌላውያንስለ ክርስቶስ ትንሣኤ አማናዊነትአስረግጠው ጽፈዋል። ለዚህም ነውወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ የመላዕክቱንየምሥራች ቃል በአድናቆት የጻፈው።“ሕያውን ከሙታን መካከል ስለምን ትፈልጋላችሁ?”ሥጋውን በከበረ ሽቶ ሊቀቡእንደመጡ ያውቃሉና። የትንሣኤውን ብሥራትዜናም በእርግጥ ቃል “ተነሥቶአል እንጂ በዚህ የለም”በማለት ሰበኩላቸው። ሴቶቹም የምሥራቹንለሐዋርያት ነገሩ። ከሐዋርያቱም ጴጥሮስናዮሐንስ ወደ መቃብሩ መጥተውተመለከቱ፤ “አዩ አመኑም”፣ እኛምሐዋርያቱ ያዩትን በእምነት አይተን፣ትንሣኤውን አመንን። “ሳያዩ የሚያምኑብፁዓን ናቸው” በማለት ጌታችንእንደተናገረው። በዚህ የምሥራች ቃልመላዕክቱ ሦስት ዐበይት ነገሮችንበአፅንዖት ተናግረዋል። ክርስቶስ ሕያው እንደሆነ - ዘላለማዊ ሕያውነቱን፤ ሞትን ድልአድርጎ መነሣቱን - “በሥልጣኑ ተነሥቷል”፤ መቃብር እንዳልያዘው - “በዚህ የለም”በማለት። ስለዚህሕያው ክርስቶስን ከሙታን መንደር፤ከመቃብር ውስጥ አታገኙትምና ስለምንበዚህ ሙታን ባሉበት ሥፍራትፈልጉታላችሁ?! እርሱ የሕያዋን አምላክነውና ከሙታን መካከል ስለምንትፈልጋላችሁ? በዚህ የለም!!! ሙታንባሉበት የመቃብር ሥፍራ ምንአለ? የበሰበሰ፣ የፈረሰ፣ ወደአፈርነት የተለወጠ ሰውነት፤ ምስጥየበላው አጥንቱ ብቻ የቀረ፣ሕይወት-አልባ ሰውነት፤ መቃብርከውጪ ሲታይ ያማረ፤ በሲሚንቶየተለሰነ በከበረ ድንጋይ ያጌጠ፤ውስጡ ግን ባዶና ጥቅምየሌለው፣ ነፍስ የተለየው አጥንትነው ያለው። እናም በዚህየለም! በሙታን ልቦና ውስጥምክርስቶስ የለም፤ ሕያው ክርሰቶስንበሙታን ልቦና ውስጥ አናገኘውም።በሕያዋን ዘንድ ክርሰቶስ አለ፤ሕያዋን በልቦናቸው መከራ መስቀሉንትንሣኤውን፤ ዕርገቱንና ዳግም ምፅአቱንያስባሉና። “ንዜኑ ሞተከ ወትንሣኤከ ቅድስት፣ ነአምን ዕርገተከ ወዳግም ምፅአተከ...” በማለትያመሰግኑታልና።
የከበረሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ “የኢየሱስሕይወት ደግሞ በሚሞት ሥጋችንይገለጥ ዘንድ እኛ ሕያዋን የሆንን፣ ከኢየሱስየተነሣ ዘወትር ለሞት አልፈንእንሰጣለንና።” ፪ኛ ቆሮ ፬÷፲፩ዳግመኛም ለኤፌሶን ምዕመናን በጻፈውመልዕክቱ “በመንፈሱ በውስጥ ሰውነታችሁ በኃይልእንድትጠነክሩ ክርሰቶስም በልባችሁ በእምነት እንዲኖር እንደክብሩ ባለጠግነትመጠን ይስጣችሁ...” በማለት ቃሉንሰምተው በትዕዛዙ ጸንተው በሚኖሩሕያዋን ልቦና ዘንድ ክርስቶስእንደሚገኝ ይነግረናል። ኤፌ ፫÷፲፮
የሰውልጅ ልቦና (ልብ) የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ እንደሆነ በተለያዩመጻሕፍት ተገልጧል። ልብ፡- የሕይወትመገኛና መውጫ ነው። ከእርሱምበሚወጣ ቃል የምሥጋና መስዋዕትየእግዚአብሔር ስም ይከብርበታል፣ ይወደስበታል። በአንጻሩ ደግሞ ልብ፡-የሕይወት መውጫ መሆኑ ቀርቶመቃብር ወደመሆን ሲለወጥ፣ ሞትንብቻ ማስተናገድ ሲጀምር፣ ሕያውነትንያጣል። የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ ተብሎምአይጠራም፤ ሕያው ክርስቶስ በውስጡየለምና። ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስክርስቶስ በመዋዕለ ስብከቱ “...በእናንተ ዘንድ የሚኖር ቃሉ የላችሁም፤ ሕይወት እንዲሆንላችሁም ወደእኔ ልትመጡ አትወዱም።” ዮሐ፭÷፴፰በማለት እንደተናገረው፤ በልቦናቸው ድንዛዜናየእንቅልፍ መንፈስ ስለፈሰሰባቸው፤ በትዕቢታቸውና ባለመታዘዛቸው ጠንቅ ልቦናቸውስለተደነፈ፤ ጥቅመኝነትና አስመሳይነት በልባቸውስለነገሠ በእነርሱ ዘንድ “የለም”ተባለ፤ ሕያው ክርስቶስ በሙታንልቦና አይኖርምና- በዚህ የለም!ጽድቅ ከዐመፅ ጋር ሕብረትየለውምና “በዚህ የለም” ተባለ።
ሐሳባቸውምድራዊ ክብራቸው በነውራቸው በሆነሰዎች ልብ፤ የክርስቶስን ሕማምናመስቀል በሚቃወሙ ሰዎች ልብ፤የአምላክ ዙፋንና ማደሪያ የሆነችውንድንግል ማርያምን፣ የክብሩ መገለጫየሆኑትን ቅዱሳንን፣ በእግዚአብሔር ፊትለምሥጋናና ለተልዕኮ የሚቆሙትን መላዕክትንበሚንቁና በሚሳደቡ ሰዎች ልብ፤የእግዚአብሔር መንፈስ ከሌለባቸው፣ ከጸጋውዙፋን ከመለኮት ብርሃን በራቁሰዎች ልብ፤ እውነትን ከተቀሙ፣በሐሰት ራዕይና በሐሰት ትምህርትተገፍተው፣ ከወንጌል መንገድ ስተውሌሎችንም በሚያቆላምጥ ቃል በሚያስቱሰዎች ልብ፤ ሃይማኖትን ክደውከሕሊናቸው በተፈጠረ መንገድ በሚመላለሱ፣የወንጌል ምስጢር ከተከደነባቸው፣ የሃይማኖትራስና ፈጻሚ፣ የሃይማኖት ሐዋርያናሊቀካህናት የሆነውን ክርስቶስን በተዉሰዎች ልብ፤ ለሥጋቸው ፈቃድብቻ በተገዙ፣ በሥራቸውና በእምነታቸውጉድለት ሙታን ተብለው ከተጠሩከሐዲያን ሰዎች ልብ ውስጥሕያው ክርስቶስ አይገኝም። ፈፅሞየለም። “ሕያውን ከሙታን መካከል ሰለምን ትፈልጋላችሁ? በዚህ የለም” የተባለውምለዚህ ነው። ሕያው ክርስቶስማበሕያዋን መካከል ተገኝቶ “ሰላም ለእናንተ ይሁን” በማለትትንሣኤውን አረጋገጠላቸው፤ በሕያዋን ማኅበርሆኖ በቀደመ ትምህርቱ የተጠራጠረውሐዋርያው ቶማስንም ሲያፀናው “ጣትህን ወደእዚህ አምጣና እጆቼን እይ፣ እጆችህንም አምጣና በጎኔአግባው፤ ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን አለው።” በማለትይነግረናል ወንጌላዊ ዮሐንስ።(ምዕ ፳÷፳፯)የሕያዋን አምላክ እንዴት ድንቀኛነው?! ታዲያ ለምንድነው አንዳንዶችሕያዉን በሕያዋን ማኅበር ሳይሆንከሙታን መንደር ለማግኘት የሚቃትቱት?!የመድኃኒታችን እግዚአብሔር በኩራት በሆኑነቢያትና ሐዋርያት መሠረትነት በታነፀችውቤተክርስቲያን ሳይሆን በመናፍቃን መንደርሕያው ክርስቶስን ሰለምን ይፈልጉታል?!“በዚህ የለም” የሚለውን ቃልየሰሙት ሴቶች ሐዋርያት ወዳሉበትወደ ሕያዋን ማኅበር ሄዱእንጂ በመቃብሩ ዙሪያ አልቀሩም።ሕያዉን በሕያዋን መካከል ያገኙታልና!ዛሬም ሕያው ክርስቶስን ከሙታንመካከል ከመቃብሩ ሳይሆን በሐዋርያትኅብረት (ማኅበር) በተመሠረተችው በአማናዊትናሕያዊት ቤተክርስቲያን ብቻ ነውየምናገኘው።
አበውበትርጓሜ እንዳስተማሩን መቃብር የሲኦልተምሳሌት ነው። መቃብር የሥጋ፣ሲኦል የነፍስ ወህኒ ነውና።ክብር ምሥጋና ይግባውና ጌታችንናመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀልላይ ሳለ ራሱን አዘንብሎነፍሱን አሳልፎ ከሰጠ በኃላየከበሩ አበው የአርማትያሱ ዮሴፍናኒቆዲሞስ የጌታችንን ቅዱስ ሥጋበአዲስ መቃብር አኖሩት። የረቀቀምስጢር እነሆ! ይህንን ምስጢርለአባቶቻችን መምህራን የገለጠላቸው እግዚአብሔርይክበር ይመስገን አሜን! በርትዕትተዋሕዶ ሃይማኖት ትምህርት፡-መለኮትየተዋሐደው ሥጋ ወደ መቃብርወረደ፤ መለኮት የተዋሐዳት ነፍስምወደ ሰዖል ወረደች። በትንሣኤውምየሥጋንና የነፍስን ሞት ሻረ፤ሥጋ ፈርሶ በስብሶ እንደማይቀርነፍስም በሲኦል እንደማትኖር አስረዳ።ዳግማዊ አዳም ሞትንና ዲያብሎስን በሥልጣኑ አሸንፎ እንደተነሣ፤ ቀዳማዊ አዳምም ከሙታን መንደር ከሲኦል ወጥቷል - በዚያ የለም። ለእግዚአብሔር ክብር ምሥጋና ይሁን!አሜን! ፩ ጴጥ ፫÷፲፰ - ፲፱ “...ስለ ዐመፀኞች አንድ ጊዜ በኃጢአት ምክንያት ሞቶአልና፤ በሥጋ ሞተ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ፤ በእርሱም ደግሞ ሄዶ በወህኒ ለነበሩ ነፍሳት ሰበከላቸው።” በእስራትናበግዞት ለነበሩት ነጻነትን አቀዳጃቸው።ይህንን የቅዱስ ጴጥሮስ ትምህርትብዙ መምህራንና ሊቃውንት ተርጉመውታል፤ ቃላቸውም አንድ ነው።ለአብነት ያህል ሁለቱን እነሆ፡-ዘኤጲፋንዮስ ምዕ ፶፮÷፴፯ “መለኮት በሥጋ አካልበመቃብር ሳለ የሥጋ ሕይወትበምትሆን በነፍስ አካል ወደሲኦል ወረደ፤ እንደዚህ ባለተዋሕዶ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ።”ዘብንያሚ ምዕ ፹፱÷፳፩ “እርሱ ክርስቶስ በሥጋበታመመ ጊዜ የታመመው እርሱራሱ እግዚአብሔር ቃል ነው።...በሕማም፣ በስቅለት፣ በሞት፣በመቀበር ጊዜ፣ እግዚአብሔር ቃልከተዋሐዳቸው ከነፍስም ከሥጋም እንዳልተለየ፤ ሰው ከመሆኑም እንዳልተለወጠ እናምናለን።”
ጌታችንናመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መግነዝፍቱልኝ፣ መቃብር ክፈቱልኝ ሳይልበሥልጣኑ ተነሣ። የጌታን መቃብርለማየት የሚመጡት ሴቶችና ሐዋርያትበትንሣኤው እንዲያምኑ ድንጋዩ ተነሥቶጠበቃቸው። ጌታችን የተቀበረበት መቃብርእንደተከፈተ የሲኦል ደጆችም ተከፈቱ፤ጌታ ከተቀበረበት መቃብር ድንጋዩእንደተነሣ አዳምን ለዘመናት ተጭኖትየነበረው የፍርድ ድንጋይ፣ አዳምንወደሲኦል ያወረደው የኃጢአትና የሞትድንጋይ ተነሣለት፤ ስለዚህ አዳምምሕያው ሆኖአል፤ ከሙታን መንደርየለም፤ ወደ ሕያዋን አምባወደ ገነት ሄዷልና። ለዘመናትተዘግቶ የነበረው የገነት በርተከፍቶለታልና። ጌታችን ተገንዞበት የነበረውየተልባ እግር ልብስ (ከፈን)መቃብር ውስጥ እንደተወው፤ አዳምታስሮበት የነበረው የሞት ሰንሰለት፤ተጠፍሮበት የነበረው የኃጢአት ገመድ፣አዳም ተገንዞበት የነበረው የዕዳበደልና የሞት መግነዝ ተፈታ፤በሲኦል መቃብር ተወው - እርሱምዲያብሎስ ነው። በጌታችን ሞትና ትንሣኤ፤ የሰው ልጅ ጥንተ ጠላቶች - ሞትና ዲያብሎስተሸንፈዋልና! ለዚህምነው፤ በቤተክርስቲያናችን ሥርዓት ከትንሣኤእስከ በዓለ ኀምሳ ይህንንየምንዘክረው፡- “ክርሰቶስ ተንሥአ እሙታን፣ በዓቢይ ኃይል ወሥልጣን፤ አሠሮ ለሰይጣን፣ አግዓዞ ለአዳም፤ ሰላም፤ እምይእዜሰ፤ ኮነ፤ ፍሰሐ ወሰላም።” መላዕክቱም “ተነሥቷል እንጂ በዚህየለም።” በማለትትንሣኤውን አበሠሩ።
ወንጌላዊውቅዱስ ማቴዎስ እንደነገረንአይሁድ የጌታችንን ትንሣኤ ለማስተባበልእንደሞከሩና እውነትን ለመቅበር እንደደከሙሁሉ ዛሬም የትንሣኤውን አማናዊነትየሚጠራጠሩና የሚክዱ ጥቂቶች አይደሉም።ክብር ምስጋና ይግባውና አምላካችንናመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለምዙሪያ በተሰበከው ቅዱስ ወንጌሉእንደተናገረው የሞተውና የተነሣው እርሱራሱ መሆኑን እናምናለን እንታመናለን። ከብዙው ማስረጃ ሁለቱንእንጥቀስ። ሉቃስ ፳፬÷፴፱ “የተቸነከሩትን እግሮቼንና እጆቼን እዩ፤ የተወጋውንም ጎኔን ተመልከቱ፤ በእኔ እንደምታዩት ለመለኮት ሥጋና አጥንት የለውም።” ራዕይ ዮሐ ፩÷፲፰ “ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ፣ ሞቼም ነበርሁ እነሆም፣ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፤ የሞትና የሲኦል መክፈቻ አለኝ።”
ከዘላለም እስራት የተፈታንበት፤ ኃጢአታችንና በደላችን ተደምስሶ አዲስ ሕይወት ያገኘንበት፤ ከሞት በኋላ ሕይወት ከመቃብርበኃላ ትንሣኤ እንዳለን በእውነትየተረዳንበት፤ የነፍሳችን ቤዛና ዘላለማዊዕረፍት እርሱ ትንሣኤና ሕይወትየሆነው መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስነው፤ የትንሣኤውም በኩር እርሱነው። በትንሣኤው የሰጠንን ሕይወትጠብቀን፤ በሃይማኖትም ጸንተን ለክብርትንሣኤ ከሚነሡት ጋር ዕድልናፈንታ አግኝተን በዘላለም መንግሥትከቅዱሳኑ ጋር ክብሩን ለመውረስያብቃን! አሜን! “ሙታንህ ሕያዋን ይሆናሉ፣ ሬሣዎችም ይነሣሉ፣ በምድር የምትኖሩ ሆይ፡- ጠልህ የብርሃን ጠል ነውና፣ ምድርም ሙታንን ታወጣለችና ንቁ ዘምሩም።”ኢሳ ፳፮÷፲፱ በማለትነቢዩ ኢሳይያስ እንዳመሰገነ እኛምለተሰጠን ሕይወትና ታላቅ ተስፋእንዘምር። ትንሣኤው አማናዊ እንደሆነሁሉ ትንሣኤን ሊሰጠን የታመነነውና። እውነት በእውነት።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
ነቢየልዑልዓይነኵሉ
በሰሜን አሜሪካ ማኅበረ በዓለ ወልድ ትምህርት ክፍል።
No comments:
Post a Comment